የኦሮሚያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ጋዜጠኛ የሆነችው ብሊሴ ቀነአ ታህሳስ 30 ቀን 2008 ዓም ከስራ ተባረረች።
ጋዜጠኛዋ በተባረረችበት ቀን በተለመደው ስራ ሰዓቷ ቢሮ ልትገባ ስትል መግቢያ በር ላይ በዘበኞች እንድትመለስ መደረጉን ኦሮሚያ ሚዲያ ኔቶርክ ዘግቧል።
ጋዜጠኛ ብሊሴ ቀነአ ከአለቃዋ ከስራ ስለመሰናበቷ የተገለጸላት ነገር አለመኖሩን የገለጸው ዜናው የስራ ባልደረቦቿ የመባረሯ ምክንያት ከሳምንት በፊት ከተፈጠረ ክስተት ጋር አገናኝተው ጥርጣሬያቸውን እንደገለጹለት ዜናው ገልጿል።
በወቅቱ ጋዜጠኞችን፣ አመራሮችንና የመንግስት ባለስልጣናትን ያሳተፈ ስብሰባ ተካሄዶ ነበር አሉኝ ምንጮቼ ያለው ኦሮሚያ ሚዲያ ኔቶርክ የስብሰባው አጀንዳ ደግሞ በመላው ኦሮሞያ እየተደረገ ያለውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለመቀልበስ እንዴት ያለ የተዋጣ ፕሮፓጋንዳ መስራት እንደሚቻል በተደረገ ወያየት ላይ ጋዜጠኛ ብሊሴ ቀነአ ለሰብሳቢዎቹ የማይመች ጥያቄ አንስታ ነበረ ሲሉ ለዜና ምንጩ እንደገለጹለት ገልጿል። አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር የኦሮሞን ህዝብ መዋሸት ኣንደማይቻልና ይህንንም
እነሱ ራሳቸው እንደሚያውቁት እንዲሁም የስራ ባልደረባዋ የነበረው ጋዜጠኛ ፍቃዱ ምርከና ለምን እንደታሰረ ግልጽ እንዲደረግ መጠየቋ ጥርስ ውስጥ አስገብቷታል ይላሉ።
↧
የኦሮሚያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ባልደረባ ጋዜጠኛ ብሊሴ ቀነአ ከስራ ተባረረች
↧