በአክሰስ ሪል እስቴት ውስጥ የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ አገር ጥለው ለሁለት አመታት የተሰደዱት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፤ ከመንግስት አካላት ጋር በተደረገ ድርድር ወደ አገራቸው ገብተው የጀመሯቸውን ስራዎች ለማስቀጠልና ከተለያዩ አካላት ለቀረቡባቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በመስማማት የካቲት 12 ቀን 2007 ዓ.ም አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።
ዛሬ ምሽት የኢትዮጵያ ቴልቭዥን በምሽት ዜና እወጃውየአክሰስ ሪል እስቴት አክስዮን ማህበር ባለቤት አቶ ኤርሚያስ አመርጋ በፖሊስ ቁጥጥር ሰር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጿል።
አቶ ኤርሚያስ ከአገር ውጪ ለሁለት አመታት በዱባይ ለመኖር የተገደዱት ድርጅታቸው አክሰስ ሪል እስቴት ክፍያ የተቀበለባቸውን ቤቶች በወቅቱ ሰርቶ ማጠናቀቅና ለቤት ገዢዎች ማስረከብ ባለመቻሉ ከቤት ገዢዎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ከቀረቡባቸው ክሶች ለመሸሽ አገር ጥለው መውጣታቸውን የሚያስታውሱት የቃልኪዳን ቲዩብ ምንጮች የአክሰስ ሪል እስቴት፣ የአክሰስ ካፒታልና የዘመን ባንክ መስራች አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፤ በሺህዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ሲባል መንግስት በሰጣቸው ያለመከሰስ ዋስትና በሚል ወደ አገር ቤት መመለሳቸው የቤት ገዥዎች ቁጣን ለማረጋጋት ለይምሰል ከአመት በኃላ በቁጥጥር ሰር መዋላቸውን ምንጮች አረጋግጠውልናል፡፡
የአክሰስ ሪል እስቴት ቤት ገዢዎችና ባለአክስዮኖች በጋራ ባቋቋሙት ኮሚቴ አማካይነት በኩባንያው ውስጥ የተፈጠረውን ቀውስ ለመፍታት ያደረጉት ጥረት ውጤት አልባ መሆኑን ተከትሎ፣ መንግስት በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ ባመለከቱት መሰረት የሚመለከታቸው የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትን ያቀፈ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጉዳዩን ሲያጣራ ቆይቷል፡፡
የአክሰስ ሪል እስቴትን ችግር ለመፍታት ያስችላል በሚል አቶ ኤርሚያስ አዘጋጅተው የላኩትን የአክሲዮን ማህበሩ ወቅታዊ ሁኔታና የቀጣይ አቅጣጫ አመላካች ሰነድና የማገገሚያ ዕቅድ ማስፈጸሚያ ዝርዝር ሃሳብ ሲመረምር የቆየው ኮሚቴው፤ የግለሰቡን ሃሳብ አዋጭነት በመገንዘብ ያወጡትን ዕቅድ ተግባራዊ ማድረግ የሚችሉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በሚል ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ቢደረግም ችግሩ ሊፈታ እንዳልቻለ ይናገራሉ፡፡
አቶ ኤርሚያስ ላይ መንግስት እጆቹን ለይምሰል የዘረጋ ይመስላል እንጂ በርካታ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር በጥቅም የተሳሰሩ በሪል እስቴት ስም መሬት የሰበሰቡና በርካታ ደንበኞችን የሚያስለቅሱ ብዙ ናቸው ይላሉ።
↧
መንግስት በሰጣቸው ያለመከሰስ ዋስትና ወደ አገር ቤት የተመለሱት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ታሰሩ
↧