Quantcast
Channel: Kalkidantube
Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

“ፍርሃት” በኢትዮጵያ ላይ የነገሰው ዋነኛ ገዥ…! _(ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ኣርኣያ፡)

$
0
0

mane
.
ስደት የፍርሃት ምንጭ ነው፤ በዚህ ላይ የተግባባን እና ወደ እውነታው የደረስን ይመስለኛል፡፡ ተሰድደው ከፍርሃታቸው በላይ ሃፍረታቸው ቀፍድዷቸው እንደተሰቃዩ የሞቱት ጥቂቶች አይደሉም፡፡ እነርሱን የኢትዮጵያ እንባ የሞትን እሳት ባህር ያርጥብላቸው፡፡ በሕይወት ካሉም የውቅያኖሱ ማዕበል ይብረድላቸው፤ ላገራቸው መሬት ያብቃቸው፡፡ በእናታቸው ፊት ቆመው የሚታዩበት ቀን ይስጣቸው፡፡
ሌላኛው የፍትርሃት ምንጭ ትጥቅ ትግል ነው፤ “ተጋዳላይም” በሉት “ፋኖ ተሰማራ” የኢትዮጵያን ገዥ ኃይል በመሳሪያ ብቻ ከሥልጣን ለማውረድ ወደ ጫካ መግባት እና ብቸኛው ከወንበር የማስወገድ መንገድ መሳሪያ ነው ብሎ ማመን ‹‹የፍርሃት ምንጭ›› ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ተስፋ የመቁረጥ ስሜት በራሱ ካመጣው የፍርሃት መንፈስ በተጨማሪ ኣመጽ እና ግርርግ እየቀሰቀሱ (ገዥ መደብን ታማኝ አድርጎ በማቅረብ) “ከኔ ውጭ አዳኝ የለሕም!!” እያለ የሚለፍፈውን ዜና አውታር ያሰለጠነው የትጥቅ ትግል መስመር ነው፡፡
በብዕር ስም መጻፍ የፍርሃት ምንጭ ነው፤ ለሚያምኑበት ዓላማ ፊት ለፊት ቆሞ አለመታዬትን የመሠለ ፍርሃት ከዬት ታመጡልኛላችሁ?
ሥንቶቻችን ቀርበን ለተቀናቃኝ ፓርቲዎች የፊት ለፊት ድጋፋችንን ሰጥተናል? ስንቶቻችን በቁርጠኝነት ሳንሰናከል እና ቀን ሳናጎድል በየፓርቲዎች ስብሰባ ላይ ተቀምጠን ሐሳባችንን፣ ድጋፋችንን፣ ተቃውሞኣችንን ሰጥተናል? በየወሩስ መዋጮ ክፍለናል? ….በዚህ ላይ ብዙ ማለት ይቻላል፡፡
97 ምርጫ ሌሎች ስኬታማ እና በታሪክ መዝገብ ተምሳሌት የሚሆኑ የሥልጣኔ እንዲሁም የመሻሻል ማንነታችን መገለጫ መሠረት ይሆናል የሚል እመነት ነበረኝ፤ የመስቀል ወፍ… የመስቀል ምርጫ ሆኖ ቀረ…
97 ምርጫን የጠላነውን ያክል እንኳ የ92ቱን የሁለት እናትና ልጅ አገር ያደረጉትን አስከፊ ጦርነት አልጠላነውም፤ 97 ምርጫ ያንገሸገሸንን ያክል የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት አላንገሸገሸንም፤ ይሕም የፍርሃታችንን መጠን የሚመዝነው ይመስለኛል፡፡
በውጭው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከ90 በመቶ በላይ የገዥው መንግስት ተቃማዊ ይመስሉኛል (የግምት ስታትስቲክስ ነው)፡፡ ይሕ ኃይል በቁጥር ሲሰላ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ስለፖለቲካው በንቃት የሚከታተለውን ሕዝብ ሳይበልጥ አይቀርም፤ ባይበልጥ እንኳ የሚያንስ አይመስለኝም፡፡ ይሕ ኃይል በፍርሃት የተሠደደን ጨምሮ በስራ እና በሕይወት መስመር ከአገር የወጣ ነው፤ ይሕ ኃይል ለሰላማዊው ትግል ቁርጠኛ ተሳትፎም ሆነ እጁን ቢያሳርፍ የታሪክ መስመር በእጅጉ በተቀየረ ነበር፤ በውጭው አገር የሚኖሩ ኢትዮጵዊያን ዋነኛው ሊማሩ የሚችሉት ነገር የእውቀተን እና የሕግን አስፈላጊነት ብቻ ነበር፡፡ ነገር ግን የውጭው ኃይል በስፋት ለጦርነት እጁን ሰጥቶ የተቀመጠ ነው፡፡ እውቀት እና ሕግ በጠበንጃ ፈጽሞ አይተከሉም፡፡ ቢተከም የአሸዋ ላይ መሰረት ናቸው፡፡
ተራራ ላይ ሆኖ ውሃ ቅዳልኝ የሚል ካለ ውሃ ቀጂው ወይ ባርያ/ሎሌ ነው አሊያም ከአንድ ሁለት ትዕዛዝ የሚያልፍ አይሆንም፡፡ በውጭው አገር ሆኖም “አገሬን ቀይሩልን”፣ “ኣመጽ መቀስቀስ”፣ “ጩኸቴን አስተጋባልኝ..” ብሎ ትዕዛዝ የለም፡፡ ካለም ከተራራው ትዕዛዝ የሚለይ አይሆንም፡፡(የሎሌ እና የጌታ ትዕዛዝ..፡፡ በሌሉነት እና በአሽከርነት እንዲሁም በሥልጣን ትግል ደግሞ አገር ፈጽሞ አትለወጥም፡፡)
የውጭው ኃይል በትጥቅ ትግል የተሰማራውን ቡድን የሚረዳውን ያክል ሰላማዊ ታጋዩን ቢረዱት ገዥው መደብ ክፉኛ በተቦረቦረ ነበር፤ ለምርጫ የሚደረግውን መስመርም ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ እቅድ፣ ግብ እና ዓላማ ነድፎ የሚንቀሳቀስ ንቁ ተሳትፎ የሚያሳይ የፓርቲ ማዕበል ቢነሳ በብዙ መልኩ ኢትዮጵያን ያግዝ ነበር፤ ይሕም ጠላቶቿን ያርቃል፣ ያስደነግጣል፣ ሕዝቦቿን ያስከብራል፤ ገዥዎቻቸውንም ያርበተብታል… ግን ምን ዋጋ ኣለው ፈሪዎች ይሕችን ኣገር መምራት ከጀመሩ 1933 ዓ.ም መሠረት ጣለ፡፡ ይሄው አሁንም ከፍቶ ይዞናል፡፡
1933 ዓ.ም ስደተኛው ንጉስ ሲነግስ፣ ባንዳ ሲወደስ፣ ኣርበኛ ሲወቀስ እና አንቱን ሲያቀረቅር… ፍርሃት በኢትዮጵያ ላይ ነገሠ!! አሁንም ከሥልጣን አልወረደም…

ጥር 2008፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

Trending Articles