Quantcast
Channel: Kalkidantube
Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

በኦሮሚያ የሕዝቡ ተቃውሞ ቀጥሏል “የታሠሩ ይፈቱ፣ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ፣ለሞቱት ቤተሰቦች ካሳ ይከፈል-VOA Amharic

$
0
0

በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው ህዝባዊ ተቃውሞ ትላንትም ቀጥሎ ውሏል።የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር እቅዱ መሰረዙን ከሁለት ሳምንታት በፊት ቢያስታውቅም ህዝቡ ማስተር ፕላኑ ተሰረዘ መባሉ የማታለያ ዘዴ ካልሆነ በቀር ለምን የታሠሩ አይፈቱም? ለምን ለሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች ካሳ አይከፈልም? ሲሉ ይጠይቃሉ ሲል ቪኦኤ ምሽት ላይ ዘግቧል።
የአርሦ አደሩ የመሬት ባለቤትነት መብት ይረጋገጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ይወገዱ የሚሉ ጥያቄዎችን ያነገቡ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ቀጥለው መዋላቸውን ይምንጮችን ጠቅሶ የዘገበው ቪኦኤ
በመላው ኦሮሚያ ለጥምቀት የወጣው ህዝብ በዘፈን ተቃውሞውን ሲያሰማ ነበር፣ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ውስጥ በተደረገ ተቃውሞ በርካታ ተማሪዎች እንደታሰሩ፣ህዝቡ ጫካ ገብቶ መደበቁን ገልጿል።በወለጋ ጃርሶ አና ነቀምት ከተማ የመከላከያ ወታደሮች ከተማዋ ብትወረርም ህዝቡ ሳይፈራቸው ሰላማዊ ተቃውሞውን ማድረግ አለመተውን የአይን እማኝ ለቪኦኤ ገልጸውለታል።እንዲሁም በሃርርጌ ጃርሶ ወረዳ አናኖ ሚሴ ከተማ የአከባቢው ነዋሪዎች እና ተማሪዎች ተቃውሞ ሲያሰሙ ውለዋል ብሏል።
ከዚሁ ጋር የተያያዘ ዜና በአርሲ ዩኒቨርስቲ አሰላ ሜዲሰን\ሕክምና ካምፓስ ከበቆጂ የመጣው ተማሪ ተስፋዬ ተሾመ የሜዲሰን ሁለተኛ አመት ተማሪ በሆዱ ላይ በተለያዩ ቦታዎች እንዲሁም ከጨለንቆ ሃረርጌ የመጣው የ3ኛ ኣመት ተማሪ ከማል አቡበከር አንገቱ አና ሆዱ ላይ በመጸዳጃ ቤት ውስጥ በስለት ተወግተው ተገኝተዋል።ጉዳት ደርሶባቸው በሕክምና አየተረዱ ይገኛሉ። ወታደሮች ወደግቢ ገብተው ተማሪውን እያስጨነቁት መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ለቪኦኤ ተናግሯል።ቪኦኤ የዩኒቨርሲቲውን ዲን ወደሆኑት ዶ/ር ሌንጮ ደውሎ ስለተፈጠረው ነገር ያናገራቸው ሲሆን “የተፈጠረውን ችግር በተመለከተ ስብሰባ ላይ ነኝ ቆይተህ ደውል” ማለታቸውን ጋዜጠኛው በተባለበት ሰዓት ሲደውል ስልካቸውን ዘግተዋል።የቪኦኤን ሙሉ ዘገባ ያዳምጡ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

Trending Articles