በእውቀቱ ስዩም አዲስ መፅሃፍ ማሳተሙን ስለሰማሁ እንዲህ እላለሁ፤ በእውቀቱን እንደ socio-political critic ወይም እንደ “ተናዳፊ ዝንብ” (gadfly) አየዋለሁ፤ ማህበረሰቡ ከድብታው እንዲነቃ፣ ህመሙን እንዲረዳ ቆንጠጥ እንደሚያደርግ ተናዳፊ ዝንብ:: (ታላቁ ግሪካዊ አንሰላሳይ ሶቅራጥስ ራሱን እንደ “ተናዳፊ ዝንብ” (gadfly) ይቆጥር እንደነበር ልብ ይሏል) የበእውቀቱ አስተዋፅዖ የኢትዮጵያን ማህበረሰብ እንደወረደ መግለፅ ወይም መፈተሽ (describing or explaining) ብቻ አይደለም፤ ፈላስፋው ካርል ማርክስ “The role of a political philosopher is not only to describe society but to change it” እንዳለው ሁሉ በእውቀቱም በስነፅሁፎቹ ማህበረሰብን ለመቀየር ተግቷል እላለሁ፡፡ (ይህ የእኔ ብቻ አተያይ ነው፤ በእውቀቱ በዚህ አገላለፄ ይስማማ አይስማማ አላውቅም፤ “እኔ ማህበረሰብን የመቀየር ተልዕኮ የለኝም” ሊልም ይችላል)፡፡
በእውቀቱ ልዩ የሚሆንብኝ “አይነኬዎችን” (taboos) በመጣስ እና በተለምዶ ገዥ ሆነው የኖሩ ድንበሮችን (boundaries) በመሻገር ስነፅሁፍን ከእስር ነፃ ያወጣ ደራሲ በመሆኑ ጭምር ነው፡፡ ለስራዎቹ የሚገባቸውን ሙሉ ስነፅሁፋዊ ነፃነት በማጎናፀፉ የኢትዮጵያ ስነፅሁፍ “ዓለማቀፋዊነትን” (universality) እንዲጎናፀፍ ጥሯል፡፡ ድርሰቶቹን ነፃ በማድረግ ራሱም ነፃ ሰው መሆኑን አሳይቷል፡፡ ስለሆነም ስራዎቹ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ ቢተረጎሙ በጠባቧ ደሴት ውስጥ በቆፈን ተቆራምዶ የተቀመጠው የሀገራችን ስነፅሁፍ በአፍሪካ ስነፅሁፍ ውስጥ የሚገባውን ቦታ እንዲያገኝ አስተዋፅዖ የሚያደርግ ይመስለኛል፡፡ Yes, Bewketu is helping Ethiopian literature to get its rightful place in what is usually called “African literature”…
ሰሞኑን ዝነኛው የናይጀሪያ ደራሲና ገጣሚ ቤን ኦክሪ (#BenOkri) ከቢቢሲ HARDtalk ጋር ያደረገውን ቃለምልልስ አዳምጬ ነበር (Mesfin Negash ቃለ ምልልሱን እንድናደምጠው በፌስቡክህ ስለጠቆምከን አመሰግናለሁ)፡፡ እናም አሁን በእውቀቱ “ኢትዮጵያዊው ቤን ኦክሪ ይሆን ይሆን?” እያልኩ መጠየቅ ጀምሪያለሁ፡፡ ቤን ኦክሪ ከአንጋፋ አፍሪካዊ ደራሲያን ጋር የተኳረፈ ደራሲ ነው፤ “ሁሌ አታለቃቅሱብን፣ ቅኝ ገዥዎች በአፍሪካዊያን ላይ ስላመጡት መዘዝ፣ ስለ አፍሪካ ችጋር፣ ሰቆቃ፣ እንባ… ብቻ እየፃፋችሁ አታልዝኑብን… ስነፅሁፍ ዓለማቀፋዊ ነው፤ የአፍሪካዊያንን ሳቃቸውን፣ ፈገግታቸውን፣ ፍቅራቸውን፣ ቀልዳቸውን፣ ተረታቸውን፣ ቸርነታቸውንም ፃፉላቸው” ባይ ነው፡፡ ተቀናቃኞቹ ደግሞ “በእንግሊዝ ነዋሪ የሆነው ኦክሪ ዓይነ-ህሊናው በቅኝ ገዥዎች ስነፅሁፍ ፍልስፍና እና ዘይቤ የተጋረደበት ደራሲ ነው” እያሉ ይተቹታል፡፡
ስለ ቤን ኦክሪ ገና ብዙ ማወቅ ቢጠበቅብኝም በኦክሪ እና በበእውቀቱ መካከል ግን ከአሁኑ አንድ ተመሳስሎሽ ታዝቢያለሁ፤ ሁለቱም በተልምዷዊው ስነፅሁፍ ዘዬ ላይ ያመፁ ደራሲዎች (rebel writers) መሆናቸውን ተረድቻለሁ፡፡ Bewketu Seyoum and Ben Okri are “rebel writers” who are in direct collision with the mainstream literature in their respective countries, Ethiopia and Nigeria, at least… የበእውቀቱ “አመፅ” በአዲሱ መፅሃፉ ምን ገፅታ ይኖረው ይሆን?
↧
በእውቀቱ ስዩምን እንደ “ናይጀሪያዊው ቤን ኦክሪ?”- (ቻላቸው ታደሰ)
↧