የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በቅርቡ ለ2016ቱ የብራዚል ኦሎምፒክ ለሚያደርገው ዝግጅት በሚል በቅርብ የስፖርት ኮሚሽን ሆነው በመጡት አቶ ሬድዋን ሁሴን የተላለፈውን መመርያ አልቀበልም በማለት ውጤታማዎቹ አሰልጣኞች ዶክተር ይልማ በርታ እና አሰልጣኝ ቶሎሳ ቆቱ ከብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝነት ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ።
አሰልጣኝ ዶክተር ይልማ በርታ ከብሄራዊ ቡድኑ የ5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር ዋና አሰልጣኝነት ወርደው የወጣቶች ብሄራዊ በድኑን እንዲያሰለጥኑ መመደባቸው ሆን ተብሎ ሞራሌን ለመንካት የተደረገ በሚል ራሳቸውን ከብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝነት ያገለሉ ሲሆን
የአዋቂ 5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር ዋና እና ረዳት አሰልጣኞች እንዲሆኑ ሁሴን ሺቦ እና ቶሎሳ ቆቱ የተመረጡ ቢሆንም
ምክትል አሰልጣኝ ሆነው እንዲሰሩ የተመረጡት ቶሎሳ ቆቱ ለአገሬ እስካሁን ያበረከትኩት ብቃት በምንም መመዘኛ በረዳትነት የሚያሰራ ባለመሆኑ ከብሄራዊ ቡደኑ ራሴን አግልያለሁ ብለዋል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን ሁለቱን አሰልጣኞች ማጣቱ ከባድ እንደሆነ ባለሞያዎች አስተያየት ይሰጣሉ።
↧
ሁለት ዝነኛ የአትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች ራሳቸውን ከአሰልጣኝነት አገለሉ።
↧