Quantcast
Channel: Kalkidantube
Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

አመፀኛው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሲያስነጥስ…? (ቻላቸው ታደሰ )

$
0
0

oil1
መላ ምት አንድ፡ “በሰለማዊ አመፅ ጊዜ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን መቆጣጠር የቻለ ኃይል ከሞላ ጎደል መላ ሀገሪቱን መቆጣጠር ይችላል፡፡” (One who controls AAU controls the soul of Ethiopia እንደማለት ነው)፡፡ ለዓመታት እንደታዘብኩት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሲያስነጥስ የመላ ሀገሪቱ ዓይኖች ያነባሉ፡፡ ስለሆነም በሃምሳ ዓመታት ታሪካችን የሦስቱም ገዥዎች ሩጫ ዩኒቨርስቲው እንዳያስነጥስ ማፈን ሆኖ ቆይቷል፡፡
በመርህ ደረጃ በየትኛውም ዓለም የገጠርና ትናንሽ ከተማዎች ሰላማዊ አመፅ ብዙ ርቀት ለመጓዝ አይቻለውም፡፡ የተማሪ ሰላማዊ አመፅም በራሱ (in and of itself ይሉታል በእንግሊዝኛው) መሰረታዊ ለውጥ አያመጣም፡፡ እንዲያውም በአሳዛኝ ሁኔታ የመክሸፍ ዕድሉ ይበዛል፡፡ ሆኖም በዓለም ታሪክ በተለይም በታዳጊ ሀገሮች በተደጋጋሚ እንደታየው የትናንሽ ከተሞችና ከዋና ከተማ ወጣ ያሉ ዩኒቨርስቲዎች አመፅ በዋና ከተማ ወደሚገኙ ተማሪዎቸ ከተዛመተ በዋና ከተማ ወደሚገኘው ህዝብ (በዋነኛነት መካከለኛው መደብ ህብረተሰብ ክፍል) በፍጥነት የመዛመት ኃይል ያገኛል፡፡ በዋና ከተማ የሚነሳ አመፅ symbolicም ሆነ practical ትሩፋቶች አሉት፡፡ የሰላማዊ አመፅ ታሪክ ቀማሪ ሁሉ ገና ብዕሩን ከማንሳቱ በኢራንና ቻይና ተማሪዎች አመፅ የሚጀምረው ወዶ አይደለም፡፡ አመፆቹ በገዥዎች ላይ bombshell ያወረዱ ስለነበሩ ነው…
በአጭሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የትላልቅ ከተማዎች መነሳሳት (uprising) ለገዥዎች ራስ ምታት ከመሆን ያለፈ አርማጌዶንን የማምጣት ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡ አዲስ አበባ ላይ ጠረጴዛው ላይ ያቀረቀረ የሮይተርስ ወይም የአሶሼትድ ፕሬስ ዘጋቢ፤ ወይም የአውሮፓ ህብረት፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ ዲፕሎማት ጆሮውን እንደ ሚዳቋ የሚቀስረው ያኔ ነው፡፡ በሀገራችን ፌደራሊዝም ስርዓት ተዘርግቶም እንኳ የሀገሪቱ ልብ ትርታ የሚለካው አዲስ አበባ ላይ በሚሆነው ነገር ነው፡፡ በተለይ በአመፅ ጊዜ አዲስ አበባ የሀገሪቱ ልብ ነች፡፡ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ሳንባ ጭምር ነች… ስድስት ኪሎና አራት ኪሎ ዩኒቨርስቲዎችም የሀገሪቱ ጥንድ ኩላሊቶች ናቸው፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሀገሪቱ ሙቀት መለኪያ thermometer ነው፡፡ በሌላ ምንም ምክንያት ሳይሆን በሀገራችን ኋላ ቀርነት ምክንያት ሌላው ዩኒቨርስቲ ሁሉ ከጣፊያ ያለፈ ሚና ላይኖረው ይችላል፡፡ ለጭፍለቃም የተጋለጠ ነው…
እስካሁንም ማንም ስለ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ወቅታዊ እንቅስቃሴ ምንም ሲል አልሰማሁም፡፡ በ1989 ዓ.ም ከጓደኞቼ ጋር በስንት ትግል ያቋቋምነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት ድምፅም አይሰማም፡፡ ፈሩን ስቶ ተንገራግጮ ከቆመ በጣም ቆይቷል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

Trending Articles