Quantcast
Channel: Kalkidantube
Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

ኢ/ር ይልቃል መንግስት ለፕሬዝደንት ኦባማ ያዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ እንደማይገኙ አስታወቁ

$
0
0

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ሀምሌ 20/2007 ዓ.ም ምሽት 1፡00 ሰዓት ላይ ቤተ መንግስት ውስጥ ለአሜሪካው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ የሚያደርገው የእራት ግብዣ ላይ እንደማይገኙ ለነገረ ኢትየጵያ ገልጸዋል፡፡

kalkidantube.com1

የራት ግብዣው ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጥሪ የተደረገላቸው ኢ/ር ይልቃል ‹‹አሸባሪ አድርጎ የሚቆጥረን ኢህአዴግ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ሲመጡ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ለማስመሰልና ዕውቅና ለማግኘት ያደረገው በመሆኑ አልገኝም›› ብለዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል አክለውም ‹‹የኢትዮጵያ ህዝብ ጭቆና እና ስቃይ ውስጥ ባለበት በአሁኑ ወቅት ኢህአዴግ የጠራው የቅንጦት ግብዣ ላይ መገኘት የህዝቡን ሰቆቃ እንደመርሳት እቆጥረዋለሁ›› ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል የአሜሪካው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ መግለጫ በሚሰጡበት ወቅት ኢህአዴግ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ነው ማለታቸው ቅር እንዳሰኛቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ኢህአዴግን በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ነው ማለት የሰላማዊ ታጋዮችን ስቃይ የሚክድና ለአምባገነኖች ይሁንታ የሚሰጥ ነው›› ሲሉ የፕሬዝደንት ኦባማን ንግግር ነቅፈውታል፡፡ ፕሬዝደንት ኦባማ የጠበንጃ ትግልን አለመደገፍን ለመግለፅ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንትን ጨምሮ ሌሎች የአሜሪካ ተቋማት ኢ-ዴሞክራሲያዊ መሆኑን አረጋግጠውት፣ መቶ ፐርሰንት ምርጫ አሸንፌያለሁ የሚልን ፓርቲ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንደተመረጠ መግለፃቸው እንዳሳዘናቸው ኢ/ር ይልቃል ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል ኢ/ር ይልቃል በነገው ዕለት የአሜሪካ ኤምባሲና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በጋራ ያዘጋጁት ስብሰባ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

Trending Articles