Quantcast
Channel: Kalkidantube
Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

ESAT Special News Feb 02 2016

$
0
0

በጋምቤላ እየተካሄደ ባለው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በየቀኑ በአማካኝ ከ10 በላይ ሰዎች እየተገደሉ መሆኑንም ኢሳት በልዩ ዜናው ዘግቧል።በጋምቤላ ሌላ የዘር ማጥራት ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን የጋምቤላ ሕዝቦች ጥምረት ግንባርን መግለጫ የጠቀሰው ዜናው ጋምባላ ባልታወጀ አዋጅ ድንጋጌ ስር መውደቋን ገልጿል። በዛሬውከአካባቢው የተገኘው አስተማማኝ መረጃ እንደሚያመለክተው በጋምቤላ ከተማ፣ በአቦል፣ በለሬ፣ በኢታንግ፣ በተሪፋም፣ በስደተኞች ካምፖች፣ በኚንኛንግ፣ አቦቦ፣ አሌሮና በሌሎችም አካባቢዎች ቀን ብቻ 2 ኑዌሮች በአጋዚ ወታደሮች ሲገደሉ፣ 5 የንዌር የልዩ ሃይል አባላት በአኝዋኮች ተገድለዋል። በአኝዋኮች በኩልም የሞቱ ሰዎች መኖራቸውንና የአስከሬን ፍለጋ ስራ እየተካሄደ መሆኑን ዜናው ገልጿል።
ጋምቤላ ከሁለት የተከፈለች ሲሆን፣ ከባሮ ወንዝ ድልድይ በላይ ኒውላንድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ኑዌሮች ሰፍረው ሲገኙ፣ በተቀራኒው ደግሞ አኝዋኮች ይገኛሉ። የአንደኛው ብሄረሰብ አባል ድልድዩን ከተሻገረ በሌላው ብሄረሰብ አባል የሚገደል መሆኑን የገለጹት ምንጮች፣ በሌሎች ወረዳዎችም በተመሳሳይ መንገድ ክፍፍል ተፈጥሮ ዜጎች እያለቁ ነው።ሙሉ ዘገባውን ያዳምጡ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

Trending Articles