Quantcast
Channel: Kalkidantube
Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

ቴድ ክሩዝ እና ሂላሪ ክሊንተን ለፕሬዘዳንትነት እጩ ምርጫ ውድድር አሸነፉ-VOA Amharic

$
0
0

በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እጩ ሆነው የሚቀርቡትን ተፎካካሪዎች የሚለየው ድምፅ በአንዳንድ ግዛቶች መሰጠት ተጀምሯል።
በአይዋ በተሰጠ ድምፅ ሪፐብሊካንን ለመወከል እየተፎካከሩ ካሉት መካከል ቴድ ክሩዝ በግዛቲቱ አሸናፊ ሆነዋል።
አወዛጋቢው ተፎካካሪ ዶናለድ ትረምፕ ሁለተኛ ሆነዋል። በመጪው ሳምንት በኒው ሃምፕሸር (New Hampshire) ከደገሙት፥ ፓርቲውን ወክለው
ሴናተር ቴድ ክሩዝ ለፕሬዘዳንትነት ይወዳደራሉ።በዲሞክራቲክ ፓርቲው በኩል ግን በቀድሞዋ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን (Hillary Clinton) እና በርኒ ሳንደርስ (Bernie Sanders) መካከል የተካሄደው ውድድር በእኩል ድምፅ ተጠናቋል። ውጤቱ በሁለቱ መካከል የሚኖረው የቅድመ ምርጫ ሂደት የረዥም ጊዜ ትግል ሊሆን እንደሚችል አመላክቷል።
በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመወዳደር የሚፈልጉ ፖለቲከኞች ሰፊ ቅስቀሳ ካካሄዱ በኋላ በየፓርቲዎቻቸው ድምፅ የመስጠት መብት ያላቸው አባላት በኩል ፓርቲውን የሚወክለውን ሰው በየግዛቶቹ የመምረጥ ሂደትን ያካተተ ነው።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

Trending Articles