Quantcast
Channel: Kalkidantube
Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

ጋምቤላ ግጭቶች ውስጥ ነች-VOA Amharic

$
0
0

ጋምቤላ ክልል ውስጥ ሰሞኑን በተፈጠረ ግጭት ብዙ ህይወት መጥፋቱን ቪኦኤ ዘገበ።
በጋምቤላ ከተማ እንዲሁም በኒለንና በኦሚንኛ ሠፈሮች፣ ስደተኞች በተጠለሉባቸው ኢታንግ እና ፑኝዶ አካባቢዎች ሁሉ በክልሉ አኝዋክና ኙወር ብሄረሰቦች አባላት መካከል ዛሬን ጨምሮ ግጭቶች እየተካሄድ መሆናቸውን ዘግቧል።
ሰሞኑን የተገደለው ሰው ቁጥር ሃያ መድረሱን ቢዘገብም የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪ ባለፉት ሁለት ወራት ብልጭ ድርግም በሚሉ ግጭቶች እስከ ሃምሣ ሰው የሚደርስ ሕይወት መጥፋቱን ይናገራሉ ብሏል፡፡ በጥቃትና በበቀል እርምጃዎች የክልሉን የገጠር መንገዶች ሥራ ቢሮ ምክትል ኃላፊን ጨምሮ የብዙ ሰው ሕይወት ጠፍቷል።
ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

Trending Articles