Quantcast
Channel: Kalkidantube
Viewing all 3774 articles
Browse latest View live

የአዲሱ ህውሀት መንግስት መጥፎ አጋጣሚ!! ( ክፍል አንድ)ኤርምያስ ለገሰ

$
0
0

1• ደስታ እና ሀዘን
ሰሞኑን ፍቺ በፍቺ ሆነናል። የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ከፊል አካል ተፈታ። ደስ አለን። የተፈቱት ካልተፈቱት ያላቸው ልዩነት ለብዙዎች ግራ ቢያጋባም!…ዛሬ ደግሞ እነ ሀብታሙ አያሌው ተፈተዋል። ይህም በግለሰብ ደረጃ ደስ የሚል ዜና ነው። ቢያንስ በቅርብ የማውቀው ሀብታሙ (” ሀብትሽ!”) ክፋ ደጉን የማታውቀው ልጁ እጁ ላይ ስታንቀላፋ፣ ወደ አልጋዋ ወስዶ ሲያስተኛት፣ ከእንቅልፏ ስትነቃ አቅፎ ሊያነሳት በመቻሉ ደስ ይለኛል። እንኳን ለዚህ አበቃህም ማለት እፈልጋለሁ።

kalkidantube.com28
በሌላ በኩል ገዥው ቡድን በምክንያት እያሰረ በምክንያት የሚፈታበት ሁኔታ ለራሱ ስልጣን መቆያ ትክክል ቢሆንም ለኢትዬጲያ የፍትህ ስርአት ምን ያህል ንቀት እንዳለው የሚያሳይ ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ነው። ሰዎች በህውሀት ላይ አደጋ ሲጋርጡ በፓለቲካ ውሳኔ ይታሰራሉ…ህውሀታዊ ምክንያት !። ገዥው ቡድን ላይ የተጋረጠው አደጋ በሌላ ጐን ሲያጋድል ደግሞ በእጁ ይዞ የሚያሰቃያቸውን ይፈታል…ህውሀታዊ የመፍታት ምክንያት!!
ሀብታሙ አያሌውና ድርጅቱ ” አንድነት” ህውሀትን በሰላማዊ ትግል ፈተና ውስጥ ለመክተት ስትራቴጂ ነድፈው ሰፊ እንቅስቃሴ ጀመሩ። የለውጥ ንፋስም በስሱ መንፈስ ጀመረ። እነ ሀብታሙ በአደባባይ ” እመኑኝ ኢህአዴግም ይወድቃል! ኢትዬጲያም ነጳ ትወጣለች!” በሚል መሪ መፈክር ገዥዎችን አስጨነቁ። የስርአቱን ባህሪያት በቅርብ የምናውቅ ሰዎች የእነ ሀብታሙ እድሜ አጭር እንደሚሆን አሳወቅን። ርግጥም ” ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም!” በሚል መርህ የሚመራው ገዥ ቡድን እነ ሀብታሙን የውሸት ክስ በማዘጋጀት ወደ ማእከላዊ ወረወረ። ” አንድነት” ፓርቲንም አፈረሰ። ኩሸቱን በመደጋገም የራሱን እውነት ፈጠረ። እነ ሱዛን ራይዝን “በ100%” ጦሽ ብለው እንዲስቁ አደረገ።
በሌላ በኩል ለውጥ በሁሉን አቀፍ ትግል ብቻ መምጣት እንዳለበት የሚያምኑ ኢትዬጲያውያን የለውጥ እንቅስቃሴውን በግላጭ ማቀጣጠል ጀመሩ። ምሁራን ዱር ቤቴ በማለት ወደ በረሀ ተመሙ። አዲስ ህልምና አዲስ አቅጣጫ ይዘው የነጳነት ትግሉን ዙር አከረሩት። እናቶች ከጣታቸው ቀለበት፣ ከአንገታቸው ሀብላቸውን እያወለቁ ትግሉን ወደማገዝ ተሸጋገሩ። የመኪናቸውን ቁልፍ ለአርበኞች አስረከቡ። በየቦታው አዳራሽ ሞልቶ እስኪፈስ ድረስ ” እኔ አርበኞች ግንቦት ሰባት ነኝ!”፣… ” እኔ አንዳርጋቸው፣ ብርሀኑ፣ ኤፍሬም፣ ንአምን… ነኝ!” የሚል ቃልኪዳን ከመግባት ባሻገር እስከ መቶ ሺህ ዶላር መዋጣት ተጀመረ። ይህን የለውጥ ስሜት በስማ ስማ ሳይሆን በአይኔ በብረቱ ተመልክቻለሁ። ቆም ብዬም ለማሰላሰል ሞክሬያለሁ።
እንደ እውነቱ ከሆነ ህውሀት ቆም ብሎ ለትክክለኛው መፍትሔ የማሰቢያው ግዜ ነበር። ይሁን እንጂ አፈጣጠሩ፣ ባህሪውና የበታችነት ስሜቱ ይህን ስለማይፈቅድለት ሌላ መፍትሔ ማሰብ ነበረበት። ከእነዚህም ውስጥ በቁጥጥሩ ስር ባሉት አንዳርጋቸው ጵጌ ስም መጵሀፍ መጳፍና እንደ ሀብታሙ አያሌው ያሉትን የፓለቲካ እስረኞች መፍታት የሚጠቀሱ ናቸው። በበረከት ፀሀፊነት በአንዳርጋቸው ስም የሚወጣው መጵሀፍ ” የሶስት ምርጫዎች ወግ!” ( ስያሜው የእኔ ነው) ገና ባይወጣም በቅርብ ቀን እንደሚወጣ ይጠበቃል። ምርቃቱም ሸራተን አዲስ አንዳርጋቸው በሌለበት ይሆናል። …እነ ሀብታሙ አያሌውም ተፈተዋል።
( ” የሶስት ምርጫዎች ወግ” በተመለከተ ” የነጳነት ትግሉና ስድስት የህውሀት ማደናገሪያ ነጥቦች” በሚለው ሀሳብ ውስጥ አካትቼ በዳላስ ቴክሳስ በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ አቅርቤ ነበር። ብዙዎች እንዲለጠፍ ስለጠየቁኝ በሌላ ክፍል እንደምመለስበት ተስፋ አደርጋለሁ።)


የአዲሱ ህውሀት መንግስት መጥፎ አጋጣሚ (ክፍል ሁለት) ኤርምያስ ለገሰ የቀድሞ ሚኒስትር

$
0
0

2• ” መውጫ መንገድ ያሳጣ ሰላማዊ ትግል”
አዲሱ የህውሀት መንግስት ሁለተኛው መጥፎ አጋጣሚ በኢትዬጲያ ሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ነው። እነዚህ ለሀይማኖታቸው ነጳነት የሚታገሉ ታጋዬች የያዙት አቋም ገዥው ቡድንን ወደ ከፍተኛ ፈተና ጐትቶ ወስዶታል። ይህን ለማለት ያስደፈረኝ ያለምክንያት አይደለም። ከልምድ በመነሳት እንጂ!

kalkidantube.com28
የዛሬ ሰባት አመት በዚህ አካባቢ የአዲስ አመት መምጫ በድርቡም የኢትዬጲያ ሚሊኒየም መግቢያ ነበር። በመላው ኢትዬጲያ በተለይም በከተሞች የቅንጅት መሪዎች ካልተፈቱ ” በሚሊኒየም ምንም የለም!” የሚሉ መፈክሮች ተስተጋቡ። ሁኔታዎች አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር (” ታላቁ መሪ” ባለማለቴ እቴጌን ከወዲሁ ይቅርታ እየጠየኩ) መውጫ መንገድ ፈለገ። “የኢትዬጲያ ሚሊኒየም የፈጠረው መልካም አጋጣሚ መጠቀም” የሚል የውስጠ ድርጅት ሰነድ እንዲዘጋጅ አደረገ። ይህ ሰነድ የታሰሩ ተቃዋሚዎችን በይቅርታ የመፍታት ፋይዳውን የሚተነትን ነበር። በዚህ ጵሁፍ ህዝቡ የይቱልን ጥያቄ ያለማቋረጥ እያነሳ ያለው ከአርቆ አስተዋይነት የመነጨ እንደሆነ ዘረዘረ። ህዝቡ ይፈቱልን የሚል ጥያቄ እያነሳ ያለው ” እኔው መርጬ ለዚህ አደረስኳቸው” ከሚል የህሊና ፀፀት እንደሆነ ተገለፀ። በመሆኑም ታሳሪዎችን በይቅርታ መፍታት ህዝቡን ከፀፀት የማውጣት ሁኔታ ስለሚፈጥር መንግስት የሚፈታበት ሁኔታ ማማተር እንዳለበት በሰፊው ተነገረ።
ታሳሪዎች የይቅርታ ጥያቄ እንዲያቀርቡ የፍርዱ ሂደት እንዲፋጠን ተደረገ። በአስቂኝና ባዶ ማስረጃ ታሳሪዎች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዲወሰን አደረገ። ( በነገራችን ላይ በመስካሪነት የቀረቡት የቀበሌ ካድሬዎች የነበሩት እነ አበባ ሽመልስ ከማል ልምምድ የሚያደርግላቸው በኢህአዴግ ቢሮ ነበር) ። የፍርድ ውሳኔውን አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እስከ እድሜ ይፍታህ አምዘገዘገው። ይህ ውሳኔ ታሳሪዎችና ቤተሰባቸው ተደናግጠው ወደ ይቅርታ ሂደቱ በፍጥነት ይገባሉ የሚል ታሳቢን የወሰደ ነበር። በወቅቱ በታሳሪዎች መስመር ያለውን ተጵእኖ በቀጥታ ከራሳቸው መስማት የምችልበት እድል ባይኖርም በአንዳንድ የቅንጅት አመራሮች እና ቤተሰባቸው ዘንድ ተጵእኖ እንዳሳደረ ሰምቻለሁ። በሌላም በኩል እንደ አንዱአለም አራጌ ያሉ አመራሮች ውሳኔውን ከመቄብ ባለመቁጠር ይቅርታ ለመጠየቅ እንዳስቸገሩ በተባራሪ ሰምተናል።
ዞሮ ዞሮ ህውሀት የገባበት አጣብቂኝ የኢትዬጲያ ሚሊኒየም የፈጠረው መልካም አጋጣሚ መፍትሔ ሊያገኝ ቻለ። ይህን አስመልክቶ አቶ በረከት በጳፈውና የህውሀትን ገድል በሚያሳየው መጵሀፋ ገጵ 233 ላይ እንደሚከተለው አስፍሮ እንመለከታለን፣
” …የፍርድ ሂደቱ ነጳ መሆን በግልፅ መታየቱና መንግስት የቅንጅት መሪዎች የተከሰሱባቸውን ወንጀሎች ከበቂ በላይ በማስረጃ አቅርቦ በማረጋገጡ ህብረተሰቡ የሰዎቹን ጥፋተኝነት በጥያቄ ውስጥ የሚጥልበት አልነበረም። በመሆኑም መንግስት በህዝቡ የቀረበው የይፈቱ ጥያቄ ፣ ማንኛውም ህዝብ በአርቆ አስተዋይነቱ የሚያደርገው… እኔ መርጬ ለእስር አበቃኃቸው ከሚል የህሊና ፀፀት ነጳ ለመውጣት በመፈለግ ያቀረበው ጥያቄ እንደሆነ ተገንዝቧል። ለዚህ አይነቱ የህዝብ ጥያቄ በጐ ምላሽ መስጠት ምንግዜም ቢሆን ግዴታው እንደሆነ የሚገነዘበው መንግስት፣ ጥያቄው የህግ የበላይነት ለድርድር ሳያቀርብ ሊመለስ እንደሚችል አምኗል። እናም በአንድ በኩል የህግ የበላይነትን እያስከበረ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የህዝብን የይፈቱ ጥያቄ ለማስተናገድ የሚችልበትን ሁኔታ ማማተር ነበረበት። በዚህ አኳኃን ነው የኢትዬጲያ ሚሌኒየም ራሱን እንደ መልካም አጋጣሚ የከሰተው” ይለናል።
እንግዲህ ከዚህ ልምድ በመነሳት የኢትዬጲያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጣቸው። ውሳኔውን መሰረት በማድረግ እስከ ሀያ አመት የሚደርስ እስራት ተፈረደባቸው። ይህ ለመጥራት የሚዘገንን ቁጥር የተበየነበት ምክንያት ታሳሪዎችን ለማስደንገጥ እና ወደ ይቅርታ ሂደቱ በፍጥነት እንዲገቡ ታስቦ እንደሆነ በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል። አንድ ግጥም አቅርበሀል የተባለ ወጣት የተፈረደበትን አመት ለተመለከተ ደግሞ በህውሀት የተጠነሰሰውን ሴራ ለመገንዘብ የእነሱን ያክል ማሰብ ከቻለ በቂው ይሆናል።
ይሁን እንጂ ይህ “የይቅርታ ይደረግልን” ሴራ ቅንጅት ላይ እንደሰራው በሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎቹ ላይ የሚሰራ አይደለም። ሲጀመር የመጀመሪያዉ ፓለቲካዊ፣ የአሁኑ ደግሞ ሀይማኖታዊ ነጳነትን በግንባር ቀደምትነት ያስቀመጠ በመሆኑ በባህሪ የተለያዩ ናቸው። ርግጥ ፓለቲካዊ መብቶች ባልተከበረበት ሀይማኖታዊ መብቶች ይከበራሉ ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ቢሆንም። ከዚህም በተጨማሪ የሀይማኖታዊ ነጳነታዊ ጥያቄዎች ለድርድር የመቅረብ እድላቸው እጅግ ጠባብ ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ነው።
ከላይ የተቀመጠውን ከግምት በመውሰድ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴው አባላት አጥፍተናል እና ይቅርታ ይደረግልን የሚሉ ከሆነ እስከዛሬ ያነሷቸው ሶስት ጥያቄዎች ( ለጊዜው የማውቃቸው) ትክክል አልነበሩም፣ አሊያም ምላሽ አግኝተዋል የሚል እንድምታ ይኖረዋል። ይህም የህውሀትን ድል አድራጊነት ከማረጋገጥ ባሻገር የኢትዬጲያ ሙስሊሞችን የሶስት አመት ትግል ውሀ ይቸልስበታል። ወደ ኃላ የመመለስና በቀላሉ የመክሰም እድል ያጋጥመዋል። የኮሚቴዎቹ አባላት ይህን በመገንዘብ ይመስላል አስደንጋጩ ብይን ሲሠጣቸው ያለምንም መደናገጥ የትግል ጵናታቸውን ለማሳየት የቻሉት። ቤተሰቦቻቸውም ቢሆን የኮሚቴው አባላት እየከፈሉ ያሉት መስዋእትነት ለሀይማኖታቸው ነጳነት መሆኑን በመገንዘብ ከጐናቸው የቆሙት።
ስለዚህ እነዚህ የኮሚቴ አባላት እንደ ቡድን የይቅርታ ጥያቄ ያቀርባሉ ብሎ ማሰብ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደመውጣት ይሆናል። በግለሰብ ደረጃ በተለያዩ ምክንያቶች የይቅርታ ሂደት ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የሚጠበቅ ቢሆንም። ይህ አማራጭ ዝግ ሆነ ማለት ህውሀት መራሹ አዲሱ መንግስት ዝም ብሎ ይቀመጣል ማለት አይደለም። በሁኔታዎች አስገዳጅነት ያለ ይቅርታ ጥያቄ ምህረት የማድረግ ግን ደግሞ በፍርድ ቤት እንዲወሰን ያደረገውን የህዝብ እንቅስቃሴ ገደብ ያለማንሳት ሊኖር ይችላል። ይህም ኮሚቴዎቹን በአይነ ቁራኛ በመከታተል የቁም እስረኛ ወደ ማድረግ መሸጋገር ይሆናል። ይህም ቢሆን ለገዥው ቡድን የሚያመጣለት አንዳችም ፓለቲካዊ ትርፍ አይኖረውም።
ግራም ነፈሰ ቀኝ የኢትዬጲያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ የአላማ ጵናት ለአዲሱ የህውሀት መራሹ መንግስት የእግር እሳት እንደሆነ ይቀጥላል። የኢትዬጲያ ሙስሊሞች የነጳነት ትግልም በኢትዬጲያ ታሪክ ውስጥ የሚኖረውን የላቀ ደረጃ እንደጠበቀ ይኖራል!…”መውጫ መንገድ ያሳጣ ሰላማዊ ትግል” ይሉሀል ይህ ነው!!

ጎጃም ውስጥ ድርቅ ገባ!!..እንሰሳትና ሰው ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው ።

$
0
0

በሀገሪቱ በተፈጠረው የዝናብ እጥረት ምክንያት በተለይ በአፋር፣ በሶማሊና በሌሎች አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ ጎጃም ውስጥም በመከሰቱ በርካታ እንሰሳት እየሞቱ መሆኑንና ሰውም ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ በተለይ ድርቁ በሶማ፣ አራራ፣ እነገ እና ሰንጠርጌ ቀበሌዎች ለበርካታ እንሰሳት ሞት ምክንያት ከመሆኑም ባሻገር ነዋሪዎችም ለከፍተኛ ችጋር ተጋልጠዋል ተብሏል፡፡

11909787_1486544044993003_2084947949_n

ድርቁ አስከፊ ደረጃ እንደደረሰ መንግስትም ማመኑን የገለፁት ነዋሪዎች ነሃሴ 7/2007 ዓ.ም የእናርጅ እናውጋ የንግድና ኢንዱስትሪ ፅ/ቤት እንዲሁም የደብረወርቅ 01 ቀበሌ ሊቀመንበር የድርቁን አስከፊነት በመግለፅ ከህዝቡ እንዳታ ማሰባሰባቸውን ስብሰባው ላይ የተገኙት ነዋሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ከእናርጅ መስቀለ፣ አረጋሚትና ሌሎችም ቀበሌዎች ገለባና ሌሎች ለከብቶች በምግብነት የሚውሉ መኖዎች ተሰባስበው በድርቅ ወደተጠቁት ቀበሌዎች መላኩን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
መንግስት እርዳታ ለማሰባሰብ የተገደደውና እርዳታ ማሰባሰብ የጀመረው በድርቁ የተጠቁት ቀበሌዎች ነዋሪዎች በዝናብ እጥረት የደረቀውን ሰብላቸውን በመያዝ፣ እንዲሁም በእንሰሳትና ሰው ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት በመግለፅ ደብረወርቅ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣታቸውና በተደጋጋሚ አቤቱታ በማቅረባቸው ነው ተብሏል፡፡ በድርቁ የተጠቁት ነዋሪዎች ስለ ድርቁ ለመንግስት ሪፖርት ለማድረግ ወደ አካባቢው ያቀኑ የግብርና ሰራተኞችንና መኪናዎቻቸውን ለተወሰነ ጊዜ በመያዝም መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸው በቶሎ ሪፖርት እንዲያደርጉ እንደጠየቁም ምንጮች ገልጸዋል፡፡
የእናርጅ እናውጋ ወረዳ እስተዳደር ለድርቁ ሁለት መቶ ሽህ ብር መመደቡንና በስብሰባው ወቅትም 28 ሺህ ብር ተዋጥቶ በቆሎ ተገዝቶ እንዲላክላቸው ቢወሰንም እስካሁን እርዳታው ለድርቁ ተጠቂዎች እንዳልደረሰላቸው የገለፁት ምንጮች ሰው የሚበላው አጥቶ፣ እንሰሳትም በዋሉበት እየቀሩ ነው ብለዋል፡፡ አንድ የደብረወርቅ ነዋሪ ለነገረ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በዝናብ እጥረት ምክንያት በድርቅ ከተጠቁት ባሻገር ሌሎች የእናርጅ እናውጋ አጎራባች ቀበሌዎች ላይም ድርቁ በመከሰቱ በሰውና በእንሰሳት ላይ ጉዳት እንደረሰ ነው ብለዋል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ

የወታደሩን ገንዘብ ህወሀቶች ይቀራመቱታል(ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)

$
0
0

ዛሬ ለኢሳት የደረሰው ጥብቅ መረጃ 11ዓመታትን ወደ ኋላ በትዝታ ወሰደኝ:: ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዋናው ጸሀፊ ቢሮ አፈትልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያጋልጠው ለሰላም አስከባሪ 11 ሺህ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሚከፈለው ደምወዝ ከ90 በመቶ በላይ የህወሀት ካዝና ውስጥ የሚገባ ነው:: በወር 13 ሚሊዮን ዶላር(500 ሚሊዮን ብር ገደማ) የወታደሩን ገንዘብ ህወሀቶች ይቀራመቱታል:: ይህን ጉዳይ የመንግስታቱ ድርጅት የሚያውቀው ይመስለኛል:: ለዚህም እኔ የተሳተፍኩበትን የሰላም አስከባሪ ዘመቻ አጋጣሚ በአስረጂነት ማሳየት እችላለሁ::

11200613_942027912509518_6866235656260785785_n

እኤአ በ2003-2004 በመንግስታቱ ድርጅት የበላይነት: በአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚነት ከተላከው የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት ጋር ወደ ቡሩንዲ ሄጄ ነበር:: ወደ 18 የምንሆን አስተርጓሚዎች ከ8 ወር እስከ 1 ዓመት ቆይተናል:: ዝርዝሩን ሌላ ጊዜ በሰፊው እመለስበታለሁ:: ከገንዘብ ጋር በተያያዘ የተፈጸመውን የህወሀቶችን ለከት ያጣ ስግብግብነትን ላጫውታችሁ::
በዘመቻው በUN ደረጃ ወርሃዊ ደምወዝ ከ1000 ዶላር ያላነሰ: የመስክ ክፍያ በቀን 60 ዶላር: የበዓል ክፍያ በአንድ በዓል 1000 ዶላር: የላብ መተኪያ: …..በጣም ብዙ ዓይነት ክፍያዎች ነበሩት:: አብዛኛው የሰላም አስከባሪ ሰራዊት አባላት በተስፋ ነበር ወደ ቡሩንዲ የተጓዘው:: እዚያ እንደደረስን ነገሮች ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆኑ:: ቃል የተገባው: በውል የታሰረው( የሚገርመው የውሉን 3 ኮፒዎች አንሰጥም ብለው እዚያው መከላከያ ግቢ ቀርቷል:: መንግስትን አምነን ነው የተጓዝነው) ክፍያ የለም:: በወር 40 ዶላር ለኪስ እየተሰጠን: ምግብና መጠጥ በአላሙዲን እየቀረበልን: እየበላንና እየጠጣን መኖር ብቻ ሆነ:: ከኢትዮጵያ ሌላ የደቡብ አፍሪካና ሞዛምቢክ የሰላም አስከባሪ ሃይሎችም ለተመሳሳይ ዘመቻ ቡሩንዲ ገብተዋል:: ለእነሱ የሚገባቸው ክፍያና ጥቅማጥቅም ሀገራቸው በባንክ አካውንታቸው የሚገባላቸው ይህንንም የሚያረጋግጥ ደረሰኝ በየወሩ እንደሚደርሳቸው በነበረን ቅርበት ተረዳን:: እኛ ግን ምንም የለም:: ስንጠይቅ ኢትዮጵያ ይጠራቀምላችኋል የሚል መልስ ከማስፈራሪያ ጋር ይሰጠናል:: በእኛና በሌሎቹ ለተመሳሳይ ዘመቻ በመጡ ሀገራት የሰላም አስከባሪው ዘመቻ አባላት መሃል ያለው የኑሮ ሁኔታ የሰማይና የምድርን ያህል የሚራራቅ ነበር:: በህወሀት ስግብግብነት የተነሳ በጣም በሚያሳፍር የኑሮ ገጽታ መቀለጂያ ሆንን:: በሰራዊቱ ውስጥ ቅሬታው ስር ሰደደ:: ተስፋው ጨለመ:: በወር 40 ዶላር እየወረወሩ እዚያ ይጠራቀምላችኋል በምትል ከቃል ያለፈ በደረሰኝ ያልተረጋገጠች ተስፋ ብቻ ይዘን በብስጭት ገፋን:: በመሃል ሲብስብን አስተርጓሚዎች ተነጋግረን ቡጁምቡራ በሚገኝ የUN ጽ/ቤት አቤቱታ ልናቀርብ ሄድን:: የተሰጠን ምላሽ ተስፋችንን ይበልጥ ገደለው:: “ስለ እናንተ የተፈራረምነው ከመንግስታችሁ ጋር በመሆኑ አይመለከተንም:: መንግስታችሁን ጠይቁ::” የሚል ወሽመጥ የሚቆርጥ ምላች ተሰጠን::
በመሃሉ መለስ ዜናዊና ሳሞራ የኑስ ሊጎበኙን ቡጁምቡራ መጡ:: ሳሞራ ሰብስቦን ችግር ካለ ንገሩኝ አለ:: ሰራዊቱ የክፍያው ነገር ሲያንገበግበው ስለከረመ ሳሞራን ሲያገኝው በየተራ እየተነሳ ጠየቀው:: ሳሞራ ጀት ሆነ:: ባለጌ አፍ እንዳለው ያረጋገጥኩት የዚያን ዕለት ነው:: የኢትዮጵያን የችግር መዓት ሲዘረዝር: መዓት ሲያወራ ቆየና ” ሰው እንደ ቤቱ እንጂ እንደ ጎረቤቱ አይኖርም:: የሌሎችን እያያችሁ እንደነሱ እንሁን ማለት አደጋ አለው:: እዚህ ገንዘብ ምንም አያደርግላችሁም:: በብር ኢትዮጵያ እየተጠራቀመላችሁ ነው:: ለሸርሙጣ ፈልጋችሁ ከሆነ ኢትዮጵያ ስትመለሱ ትደርሱበታላችሁ…..” እያለ ወረደብን:: ሰራዊቱ ቅስሙ ተሰበረ:: ብዙ የምንሰራው ስራ አለ:: ትምህርት ቤት እንገነባለን:: ….እያለ ተንዘባዘበ:: የዚያን ዕለት ሌሊት ከአምቦ የመጣ የሰራዊቱ አባል በታጠቀው መሳሪያ ራሱን አጠፋ:: ባርቆበት ነው የሚል ሪፖርት እንድናዘጋጅ በህወሀት የጦር አዛዦች መመሪያ ተሰጥቶን የውሸት ሪፖርት አዘጋጅተን ለUN ተላከ:: ይህ የሆነበትም ራሱን ካጠፋ UN ካሳ አይከፍልም:: እርግጠኛ ነኝ በዚህ የተገኘውን በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር ዶላር ህወሀቶች ኪስ ገብቷል::
ወደ ኢትዮጵያ ስንመለስ እየተጠራቀመላችሁ ነው እየተባለ ስንሸነገል የከረምንበትን ገንዘብ ሊሰጡን ተዘጋጁ:: ለአንድ የሰላም አስከባሪ ሰራዊቱ አባል በትንሹ ከ250ሺህ ብር በላይ ወይም በወቅቱ ምንዛሪ 10ሺህ ዶላር መከፈል ነበረበት:: በጣም የሚያሳፍር የሚያስደነግጥ ነገር ነበር የጠበቀን:: እንደ ቆይታ ጊዜ ከ15ሺህ እስከ 25ሺህ የኢትዮጵያ ብር ሰጥተው አሰናበቱን:: ከእያንዳንዳችን ከ200ሺህ ብር በላይ ህወሀቶች ተቀራመቱት:: …በሌላ ጊዜ በስፋት እመለስበታለሁ::

የፖለቲካ ምሁር ጀዋር ሙሃመድ የሙስሊሙን ኮሚቴዎችና የዲያስፖራ ቀንን በማስመልከት ከቢቢኤን ያደረገው ቆ ይታ

ሀብታሙ አያሌው ዛሬ ከቂሊንጦ መውጣት ሳይችል ቀረ ሰኞ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል (ኤልያስ ገብሩ)

$
0
0

ትናንት ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት፤ ከተከሰሱበት የሽብርተኝነት ወንጀል በነጻ ከተሰናበቱት አምስት ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆነውና የቀድሞ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው ሀብታሙ አያሌው ከታሰረበት ከቂሊንጦ እስር ቤት በዛሬው ዕለት መውጣት እንዳልቻለ ለማወቅ ተችሏል፡፡

11351148_1446067909027392_3179316798669718355_n

የሀብታሙ ባለቤት ወ/ሮ ቤተልሄም እንደገለጸችው ከሆነ፤ ለፍቺ የሚያስፈልጉ ሕጋዊ ሂደቶችን አስተካክለው ከዛሬ ከሰዓት ጀምሮ በቂሊንጦ ቢገኙም ባለቤቷ መውጣት አልቻለም፡፡ ወ/ሮ ቤተልሄም አያይዛም እስከ ምሽት 12፡45 ሰዓት ድረስ በቂሊንጦ የጊዜ ቀጠሮ እስር ቤት በር ላይ ቆመው የሀብታሙን መውጣት ቢጠባበቁም ሀብታሙ ሳይመጣ በመቅረቱ ወደመኖሪያ ቤታቸው መመለሳቸውን አስረድታለች – ‹‹ሰኞ ይወጣል ብለን ተስፋ እናደርጋለን›› በማለት፡፡
በትናንቱ የፍርድ ቤት ውሎ፤ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አመራር የነበረው ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና ፓርቲ አመራር አባል አብርሃ ደስታ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባል የሺዋስ አሠፋና አብርሃም ሰለሞን ክሱን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ፣ በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ አብረው የተከሰሱ አምስት ተከሳሾች ግን እንዲከላከሉ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

Bekenat Mekakel Drama Part 17 በቀናት መካከል ክፍል 17

$
0
0

Bekenat Mekakel Drama Part 17_
Bekenat Mekakel Drama Part 17 በቀናት መካከል ክፍል 17_Bekenat Mekakel Drama Part 17_

Abrham Belayneh – Nafkote – (Official Audio Video) – New Ethiopian music 2015

$
0
0

Abrham Belayneh – Nafkote – (Official Audio Video) – New Ethiopian music 2015>>>>>>> Abrham Belayneh – Nafkote – (Official Audio Video) – New Ethiopian music 2015

Zema & Getim – Abrham Belayneh


Interview with Dr Getachew Metaferia – Pt II-SBSAmharic

$
0
0

Interview with Dr Getachew Metaferia – Pt II – SBS Amharic-ዶ/ር ጌታቸው መታፈሪያ፤ የ “Ethiopia and the United States: History, Diplomacy, and Analysis” መጽሐፍ ደራሲ ስለ ኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ ታሪካዊ ግንኙነቶችና የፕሬዚደንት ባራክ ኦባማን የኢትዮጵያ ጉብኝት አስመልክተው ይናገራሉ።

PM Netanyahu was detered from attacking iran by (ALEMNEH WASSE NEWS)

$
0
0

PM Netanyahu was detered from attacking iran by (ALEMNEH WASSE NEWS)..,….PM Netanyahu was detered from attacking iran by (ALEMNEH WASSE NEWS)

Chelsea in £69m Pogba deal

$
0
0

Chelsea have agreed a £69million deal to sign Paul Pogba from Juventus, according to reports.

kalkidantube.com51
The Blues are looking to make a couple more world class additions to their squad after a sluggish start to the new Premier League season.

And after rumours about a deal for Pogba yesterday, the Sun says Chelsea have now agreed a fee for his services.

The paper says the deal would be worth £69million – making him the most expensive signing in British football history.

Pogba, who was linked with Manchester City earlier in the summer, is also a target for Real Madrid and Barcelona.

Latest Full Episode of Balageru Idol August 22, 2015

$
0
0

Balageru Idol Latest Full Episode of Balageru Idol August 22, 2015…………..Latest Full Episode of Balageru Idol August 22, 2015

Bethelhem Dagnachew – Fikir Yilegnal New Ethiopian Music 2015 (Official Video)

$
0
0

Bethelhem Dagnachew – Fikir Yilegnal New Ethiopian Music 2015 (Official Video)……Bethelhem Dagnachew – Fikir Yilegnal – New Ethiopian Music 2015 (Official Video)

በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተደብቆ ስዊድን የገባው ወጣት ተናገረ

$
0
0

ሰሞኑን በኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞ አውሮፕላን በእቃ መጫኛ ውስጥ ተደብቆ በስዊድን ጥገኝነትን የጠየቀው ኢትዮጵያ በአየር መንገድ ውስጥ በአንድ ብሄር የበላይነት የሚደርሰው በደልና ግፍ ለህዝብ ለማጋለጥ ሲል ድርጊቱን መፈጸሙን ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ አስታወቀ።

11896042_942631525782490_6593590868298073408_n
የ 24 አመቱ ወጣት ይርጋሸዋ ማሽላ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ለመናገር የሚከብድ የአንድ ብሄር የበላይነት ሰፍኖ እንደሚገኝ እና በአየር መንገዱ ውስጥ ለመናገር የሚከብድ የአንድ ብሄር የበላይነት ሰፍኖ በሚገኝ እስር ቤት ለሁለት ቀን መታሰሩን ገልጿል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ የእቃ ማጓጓዣ ክፍል ውስጥ ሰራተኞች የነበረው ወጣት ይርጋሸዋ በስራው ላይ ያለ እስክሪን ፍተሻ ያለፈ የአንዲት ኢትዮጵያዊ ሻንጣ ተከፍቶ መገመት የሚቸግረው ዶላር መታየቱንና የጸጥታ ሀይሎች ሻንጣውን አውቀህ ነው የከፈትከው በሚል ለእስር እንደዳረጉት አስረድቷል። ከኢትዮጵያ ሊወጣ የነበረውን ሻንጣ መከፈት ተከትሎም ወጣቱ በአየር መንገድ ውስጥ በሚገኝ ልዩ እስር ቤት ለሁለት ቀን ያለ-ምግብ እና ውሃ ታስሮ መቆየቱን በቃለ ምልልሱ ገልጿል። አቶ ጦናይ የተባሉ የአየር መንገዱ የጸጥታ ክፍል ሀላፊ ወጣቱ ያየውን ሁኔታ ለሌላ ሰው ከተናገረ በቤተሰቡ ላይ አደጋ እንደሚደርስበት አሳስበውት እንደነበር አመልክቷል። ለ 8 ሰአታት ያህል በአውሮፕላኑ የእቃ መጫኛ ክፍል ውስጥ ተደብቆ በስዊድን የፖለቲካ ጥገኝነትን ያቀረበው የአየር መንገዱ ሰራተኛ ትምህርታቸውን በአግባቡ ያላጠናቀቁ የአንድ ብሄር ተወላጆች በአየር መንገዱ ዋና ዋና ቦታዎች ተመድበው እንደሚገኙም ገልጸዋል። በአየር መንገዱ ለሁለት አመታት ያየውን ግፍና በደል እንዲሁም የአንድ ብሄር የበላይነት በመቃወምና ጉዳዩን ለህዝብ ለማጋለጥ ሲል ህይወቱን አደጋ ላይ በሚጥል ሁኔታ ስደት መምረጡን በቃለ ምልልሱ አስረድቷል; የባለስልጣናት ቤተሰቦችና የቅርብ ጓደኞችም ከሀገር ይዘው የሚወጡትና ወደ ሀገር ይዘው የሚገቡት ሻንጣ ምንም ፍተሻ እንደማይደረግበት የፖለቲካ ጥገኝነቱን አቅርቦ የሚገኘው ወጣት ይርጋሸዋ አክሎ ገልጿል። በጉዞው ወቅት በእቃዎች መጫን ምክንያት መጠነኛ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር የተናገረው የአየር መንገዱ የቀድሞ ሰራተኛ ህይወቱ በተአምር ተርፎ በኢትዮጵያ ውስጥ በገዢው የኢህአዴግ መንግስት የሚፈጸመውን በደል ለሀዝብ ይፋ ለማድረግ በመብቃቱ ደስታ እንደተሰማው ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ-ምልልስ ገልጿል።ምንጭ ኢሳት

the heart – breaking saga of an ethiopian mother at jeda hospital in S.ARABIA.

$
0
0

A 40-year-old Ethiopian mother, whose son was totally paralyzed more than nine years ago as a result of a botched operation at one of Jeddah’s leading hospitals, has rejected SR2.4 million in compensation awarded to her by a special committee of the Health Ministry.


Meleket Drama (መለከት) – Episode 23

$
0
0

Meleket Drama (መለከት) – Episode 23,Meleket Drama (መለከት) – Episode 23,,,,Meleket Drama (መለከት) – Episode 23,,,Meleket Drama (መለከት) – Episode 23,

Ethiopian Comedy Series Betoch Part 109

$
0
0

The Latest Episode of Ethiopian Comedy Series Betoch Part 109 is Finally Here…የቤቶች ተከታታይ የEBC አስቂኝ ድራማ ክፍል 109 እነሆ….Ethiopian Comedy Series Betoch Part 109

አሽሊ ማዲሰን –የሚሊዮኖችን ትዳር ስታናጋ ትሰነብታለች! (Reason for Ethiopia)

$
0
0

አሽሊ ማዲሰን – የሚሊዮኖችን ትዳር ስታናጋ ትሰነብታለች!
• “አሽሊ ማዲሰን፣ የድረገፅ ስም ነው” – ለባለትዳሮች የተዘጋጀ ድረገፅ።
• ለድብቅ የፆታ ግንኙነት፣ ከ33 ሚ. በላይ ሰዎች የ‘አሽሊ’ ደንበኛ ሆነዋል።
• የእነዚህ ሁሉ ደንበኞች መረጃ ተሰርቆ፣ ሰሞኑን በኢንተርኔት ተለቋል።
• ማዕበል ነው። የሚሊዮኖች ጉድ እየወጣ፤ ስንትና ስንት ቤተሰብ ይናጋል!
• በየአገሩ፣ የፍቺ ጥያቄ እየተነሳ ነው። በርካቶች ከስራ ይባረራሉ። ሌላም…
“አሽሊ”… ከካናዳ እስከ ደቡብ አፍሪካ፣ ከአሜሪካ ኋይት ሃውስ እስከ ሳዑዲ አረቢያ፤ ከእንግሊዝ እስከ ኮሎምቢያና ብራዚል፣… 46 አገራትን አዳርሳለች።

1a
አመጣጧ ከካናዳ ነው – “አሽሊ ማዲሰን” በተሰኘው ድረገፅ።
መለያ ባህሪዋስ? “ዝሙትን የምታስፋፋ፣ ይሉኝታ ቢስ ባለጌ ናት” ብለው የሚያወግዟት ይበዛሉ።
እሷ ግን፣ “ግልፅነት ባህሪዬ ነው” ትላለች። ዋና መፈክሯም፣ እንዲህ ይላል፡
“Life is short. Have an affair.”
(“ሕይወት አጭር ናት፤ ድብቅ የፆታ ግንኙነት ይኑራችሁ”)።
‘የፆታ ግንኙነት ለመፍጠር ያገለግላሉ’ ተብለው የተዘጋጁ በርካታ ድረገፆች ቢኖሩም፣ “አሽሊ ማዲሰን” ለየት ትላለች። ለባለትዳሮች ታስባ የተዘጋጀች ድረገፅ ናት – ያው፣ ከትዳር ውጭ መሄድ ለሚፈልጉ ሰዎችን የምታስተናግድ።
(የ‘affair’ ማሳለጫ… በአማርኛ ምን ቢባል ይሻላል? ደስታ ተክለወልድ ቢጠየቁ፣ “አስወሻሚ፣ አቃጣሪ” ወይም ደግሞ፣ “መወሸሚያ”፣ “መቃጠሪያ”፣ “መወስለቻ” ብለው ሳይጠሩት አይቀሩም። ከመዝገበ ቃላት የተገኙ ናቸው። “አስመንዛሪ” እና “መመንዘርያ” ቢባልስ? ምናልባት፣ ማመንዘር የሚለው ቃል፣ ከምንዛሬ ጋር የሚገናኝ ከሆነ ማለቴ ነው – አንድ የነበረውን፣ ወደ ሁለት፣ ወደ ሦስት መመንዘር)።
ለማንኛውም፣ አሽሊ ማዲሰን በሚል የሴት ስም የተከፈተው ድረገፅ፣ ገና ከመነሻው ብዙ ተወግዟል። ከዚያ ወዲህም፣ ከአወዛጋቢነትና ከመዓት የውግዘት ወርጅብኝ አምልጦ አያውቅም። ግን፣ በዚህ የተጎዳ አይመስልም። እንዲያውም፣ በስፋት ለመታወቅ ሳይጠቅመው አልቀረም። የተመዝጋቢ ደንበኞች ቁጥር እየተበራከተ፣ ገቢውም እየጨመረ ነው የመጣው።
• የድረገፁ አሰራር፡
ድረገፁ፣ የደንበኞቹን ማንነትና የመልዕክት ልውውጥ በሚስጥር የሚደብቅ ቢሆንም፣ አሰራሩ ግን፣ እንደ ሌሎች ‘ማህበራዊ ድረገፆች’ (እንደነ ፌስቡክ አይነት) ነው ተብሏል። ሰዎችን ያገናኛል። ደንበኛ ለመሆን፣ ‘ኢሜይል’ እና ‘ፓስወርድ’ መሙላት፣ ማንነትንና ፍላጎትን የሚገልፅ ‘ፕሮፋይል’ መፃፍ… ወዘተ ያስፈልጋል።…
እዚህ ላይ፣ ‘ኢትዮጵያውያን ደንበኞች ይኖሩበት ይሆን እንዴ?’ የሚል ጥያቄ መፈጠሩ የማይቀር ነው።
ግን፣ አይዟችሁ፣ ኢትዮጵያውያን እዚህ አገር ሆነው፣ የ‘አሽሊ’ ደንበኛ ሊሆኑ የሚችሉበት እድል ጠባብ ነው። ለምን ብትሉ፣ ለደንበኝነት መመዝገብ ብቻውን ዋጋ የለውም። “የአሽሊ” ደንበኞች፣ የፅሁፍ መልዕክት መለዋወጥና ግንኙነት መፍጠር የሚችሉት፣ በክፍያ ነው።
ክፍያውን፣ በክሬዲት ካርድና በኢንተርኔት የሚሰበስበው ይሄው ድረገፅ፣ ከ33 ሚሊዮን ከሚበልጡ ደንበኞቹ፣ ባለፈው አመት ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እንዳገኘ smh ዘግቧል። ከአመት አመት፣ ገበያው እየደራለት ነበር ማለት ነው። ዘንድሮ ግን፣ አልሆነውም።
• ለአመታት የተጠራቀመ ‘ጉድ’
የድረገፁ ባለቤቶችና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞች፣ እጅግ የሚፈሩት ነገር ነው፣ አሁለን በእውን የደረሰባቸው። የደንበኞች የኤሜይል አድራሻ፣ ስም፣ የስልክ ቁጥር፣ የመኖሪያ አድራሻ፣ የፅሁፍ መልክእክት ልውውጥ፣ የክሬዲት ካርድ መለያ ቁጥር፣ የክፍያ መጠን… ምናለፋችሁ?
“በድረገፁ ውስጥ፣ በሚስጥር ተይዞ የነበረ መረጃ በሙሉ ተሰረቀ” የሚል ዜና ሲዘገብ፣ ምንኛ እንደሚደነግጡ ለመገመት ያስቸግራል። ለብዙዎቹ፣ ‘ምድር ሰማዩ ዞረባቸው’ ቢባል ይሻላል። ዜናው በየቀኑ በቲቪ ሲደጋገም፣ ምን ያህል እንደሚሳቀቁ አስቡት – ከዛሬ ነገ ‘ጉዴ ይታወቃል፣ ቤተሰቤ ይፈርሳል፣ የአገር መሳለቂያ እሆናለሁ’ ብለው እየተጨነቁ፣ መች እፎይታና እንቅልፍ ይገኛል!
• መራራ መርዶ
ዘጋርዲያን እንደዘገበው፣ አንዲት አውስትሪያዊት፣ የባሏ ፀባይ እንደተቀየረባት ስትገልፅ እንዲህ ብላለች።
“ይሄ ዜና ከተሰማበት እለት ጀምሮ፣ የባለቤቴ ሁኔታ ተቀይሯል። በሆነ ባልሆነ ነገር፣ ይደነብራል። ቀልብ ርቆታል። ምናልባት የአሽሊ ደንበኛ እንዳይሆን ጠረጠርኩ። እንዴት ነው ማረጋገጥ የምችለው?”
በቀጥታ የሚተላለፍ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ በስልክ ደውላ ነው፣ ይህንን የተናገረችው። ሰሞኑን ማክሰኞ እለት። የባለቤቷን ስምና የኢሜይል አድራሻ ጠየቋት። ነገረቻቸው። ጊዜ አልፈጀባቸውም። በኢንተርኔት የተለቀቀው መረጃ ውስጥ፣ የሰውዬው ስምና አድራሻ አለ። እንዴት ይንገሯት? “ይቅርታ፣ በጣም እናዝናለን። የባሌበትሽ ስም አግኝተነዋል።
ባለቤቷ፣ ከትዳሩ ውጭ የፆታ ግንኙነት ለመፍጠር፣ ‘የአሽሊ ማዲሰን’ ደንበኛ ሆኗል ማለት ነው። በንዴትና በእልህ ድምጿ እየተቆራረጠ፣ ስልኩን ጠረቀመችው። የዚህ ጉድ መዘዝ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም። ኢንዲፐንደንት እንደዘገበው፣ በበርካታ አገራት፣ የፍቺ ጥያቄዎችና ክሶች ከየአቅጣጫው መምጣት ጀምረዋል።
• የአሽሊ ደንበኞች በየአገሩ
በአሜሪካ፣ ከኋይት ሃውስ ሰራተኞችና ከአቃቤ ህጎች ጀምሮ፣ እስከ ማዘጋጃ ቤት ሰራተኞችና ወታደሮች… ከ10 ሺ በላይ ሰዎች፣ የአሽሊ ደንበኞች መሆናቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል – ኤፒ።
ከሁሉም በላይ ግን፣ ካናዳ፣ ዋናዋ ‘የአሽሊ መናሃሪያ ናት ማለት ይቻላል። በኦታዋ ከተማ፣ ከ100 ባለትዳሮች መካከል 20ዎቹ፣ የድረገፁ ደንበኞች እንደሆኑ ሲኤንኤን ዘግቧል። በእንግሊዝና በአውስትራሊያ፣ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የአሽሊ ደንበኞች አሉ።
ከሁሉም ከተሞች በላይ ብዙ የአሽሊ ደንበኞች የተመዘገቡበት ከተማ ግን፣ የብራዚሏ ሳኦ ፖሎ ናት – ከ370 ሺ በላይ። አየርላንድ፣ ስፔን፣ ኮሎምቢያ፣ ሳዑዲ አረቢያ ወዘተ…።
ምንም እንኳ፣ ከትዳር ውጭ መሄድ፣ አብዛኛውን ጊዜ በወንጀል የሚያስከስስ ባይሆንም፣ የጦር ሃይል አባላትን ግን፣ ለእስር ሊዳርግ ይችላል ተብሏል። ከስራ የሚባረሩም ይኖራሉ። “የመንግስት መስሪያቤት ኮምፒዩተሮችን፣ አላግባብ ተጠቅመዋል” የሚል ቅጣትም ይመጣባቸዋል።
ይሄ ሁሉ መዘዝ፣ ኑሮን የሚያናጋ ቢሆንም፣ በዚህ አያበቃም። ትዳራቸውና ቤተሰባቸውም፣ ይታመሳል። ይሄም ብቻ አይደለም።
• የሚያሳቅቅ ሚስጥር፣ የደንበኞች የፅሁፍ ልውውጥ
መረጃው ሲሰራጭ፣ “ዘመድና ወዳጅ፣ ጎረቤትና የስራ ባልደረባ ሁሉ፣ መቀለጃ ያደርገኛል” የሚለው ጭንቀት፣ ቀላል እንዳይመስላችሁ።
‘እንዲህ አይነት ሴት ትመቸኛለች’፣ ‘እንዲያ አይነት ወንድ ይማርከኛል’፣ ‘ይሄኛውና ያኛው የወሲብ አይነት እወዳለሁ’… እንዲህ በጥቅሉና በድፍኑ ሳይሆን፣ በዝርዝርና በተደጋጋሚ… የድረገፁ ደንበኞች የፃፏቸው መልዕክቶች፣ በይፋ ሲወጡ አስቡት።
ምን ይሄ ብቻ! በአንዳንድ አገራት ደግሞ፣ ከትዳር ውጭ መሄድ፣ ለሞት ቅጣት ይዳርጋል።
በአጭሩ፣ ሰሞኑን በኢንተርኔት የተለቀቀውን መረጃ፣ እንደ አደገኛ ማዕበል በመቁጠር፣ አለማቀፍ የሚዲያ ተቋማት ሲዘገቡት የሰነበቱት፣ የሰዎች ገመና ሲጋለጥ የማየት ፍላጎት ስላለባቸው አይደለም። … እሺ፣ በከፊል፣ በተወሰነ ደረጃ፣ የሰዎችን ገመና የማየት ዝንባሌም ሊኖር ይችላል።
ነገር ግን፣ ጉዳዩ፣ ከ30 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የሚነካ፣ ኑሮንና መተዳደሪያ ስራን፣ ትዳርንና ቤተሰብን ሁሉ ሊያናጋ የሚችል ጉዳይ በመሆኑ ጭምር ነው። በዚያ ላይ፣ አብዛኛው መረጃ፣ … የኢሜይልና የፅሁፍ ልውውጥ ብቻ ሳይሆን፣ የትምህርት ውጤት፣ የጤና ምርመራ፣ የባንክ ሂሳብ ወዘተ፣… በኮምፒዩተርና በኢንተርኔት በሚከማችበትና በሚሰራጭበት በዛሬው ዘመን፣ አንዳች መረጃ ተሰርቆ ሲሰራጭ፣ ብዙዎቹን ማሳሰቡ አይቀርም።
• መረጃውን ማን ሰረቀ? ከዛቻውና ማስጠንቀቂያው ጋር።
የ‘አሽሊ ማዲሰን’ ድረገፅ ሚስጥራዊ መረጃ የተሰረቀው፣ በ‘impact team’ ነው ብሎ መናገር ይቻላል። ግን ብዙም ትርጉም የለውም። ‘ኢምፓክት ቲም’ ማን እንደሆነ አይታወቅም። ደግሞም አይገርምም። የሰዎችን የግል መረጃ መበርበር ወይም መስረቅ፣ ለእስር የሚዳርግ ወንጀል ስለሆነ፣ ‘መረጃ ሰርቄያለሁ’ ብሎ በግልፅ የሚመጣ ሰው አይኖርም – ብዙውን ጊዜ።
ስለዚህ፣ የድረገፁን መረጃ ማን እንደሰረቀ አይታወቅም – ‘impact team’ ከሚለው ስያሜ በቀር። በዚህ ስያሜም ነው፣ ከአንድ ወር በፊት፣ የማስጠንቀቂያ መልእክት ወይም ዛቻ የተላለፈው።
“የድረገፁ መረጃ፣ በሙሉ እጃችን ውስጥ ገብቷል። ድረገፁ፣ በአንድ ወር ውስጥ ካልተዘጋ፣ መረጃውን በኢንተርኔት እናሰራጫለን” የሚል ዛቻ መልእክት ይዟል ማስጠንቀቂያው።
ከዚህ በኋላ ነው፣ የብዙ ሚሊዮን ሰዎች፣ የእለት ተእለት ሕይወት በሽብር የተዋጠው። “እያንዳንዷ ቀን”፣ “ረዥም የጭንቀት ቀን” እየሆነችባቸው፣ ይሄውና ሰሞኑን፣ አንድ ወር ደፈናቸው። የፈሩት አልቀረም። ዛቻውም ዛቻ ብቻ ሆኖ አልቀረም።
ለአመታት የተጠራቀመው፣ የደንበኞች “ጉደኛ” የመረጃ ክምር፣ ከማክሰኞ እለት ወዲህ እየተለቀቀ ነው – (የብዙ ጊጋ ባይት የመረጃ ክምር)። በክምሩ ውስጥ የታጨቁት፣ ዝርዝር መረጃዎች ግን፣ ገና በስፋት አልተሰራጩም። በጥቂት በጥቂቱ፣ እየተመዘዘ ነው ሲናፈስ የሰነበተው። ከዚያም፣ ዝርዝሩ እየተመነዘረ ሲስፋፋ ይሰነብታል።
እስካሁን፣ ገና ጫፉ ብቻ ነው የታየው። እንዲያም ሆኖ ከወዲሁ፣ የብዙ ሰዎች መደበኛ ኑሮ፣ ቤተሰብና ስራ መናጋት ጀምሯል። የ33 ሚሊዮን ሰዎች፣ እልፍ መረጃ በስፋት ሲሰራጭስ? ገና ምኑም አልተነካም ማለት ይቻላል። በጥቅሉ፣ “አሽሊ ማዲሰን – የሚሊዮኖችን ትዳር ስታናጋ ትሰነብታለች!” ቢባል ይቀላል።
• (በመጨረሻም ሦስት ነጥቦች)
1. የድረገፁ ፈጣሪ ምን ይላል?
ድረገፁ፣ ‘አሽሊ ማዲሰን’ ተብሎ በሴት ስም የተሰየመ ቢሆንም፣ መስራቹ ግን ወንድ ነው። ለዚያውም፣ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት። እሱ እንደሚለው ከሆነ፣ የድረገፁ ደንበኛ አይደለም። ከትዳሬ ውጭ አልሄድም ብሏል።
ሌሎችን ለምን ታደፋፍራለህ ተብሎ ሲጠየቅም፣ “አላደፋፈርኩም። ከትዳር ውጭ መሄድ፣… ከጥንት ጀምሮ የነበረ ነገር ነው። ድሮም ቢሆን፣ የፆታ ግንኙነት ለመፍጠር ከሚሞክሩ ወንዶች መካከል፣ 25 በመቶ ያህሉ ባለትዳሮች እንደሆኑ ይታወቃል። እነዚህን ሰዎች የሚያገለግል ድረገፅ ነው የፈጠርኩት” በማለት ይመልሳል።
2. ከሴቶች ይልቅ ወንዶች?
ድረገፁ፣ ወንድ ደንበኞችንና ሴት ደንበኞችን ያስተናግዳል ቢባልም፣ አብዛኞቹ ደንበኞች ወንዶች ናቸው ተብሏል። 30 ሚሊዮን ያህሉ ወንዶች፣ 3 ሚሊዮን ያህሉ ሴቶች እንደሆኑ ይገመታል።
የሴቶቹ ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ፣ አብዛኞቹ ወንዶች የተመኙትን አይነት ግንኙነት የመፍጠር እድላቸው አነስተኛ ነው፤ በከንቱ ነው የሚደክሙት ተብሏል። እንዲያውም፣ ድረገፁ ብዙ የሴት ደንበኞች እንዳሉት ለማስመሰል፣ በሺ የሚቆጠሩ የውሸት ደንበኞችን እንደፈጠረ ተዘግቧል።
3. ትንሽ በአማርኛ…
“affair” … ለሚለው ቃል፣ በአማርኛ ብዙ ተቀራራቢ ቃላት ሳይኖሩ አይቀርም። “መሄድ”፣ “ሂያጅ”፣ “የስርቆሽ” ከሚሉ ለዘብተኛ ተቀራራቢ ቃላት ጀምሮ፣ እስከ “መራር” ቃላት ድረስ ይዘልቃል። ማመንዘር፣ መወስለት፣ መማገጥ፣ ውሽማ መያዝ…
(የደስታ ተክለወልድ መዝገበ ቃላት፣ ለሴትም ሆነ ለውንድ፣ “ውሽማ” እንደሚባል ጠቅሰው፣ ቃሉ “ውሻማ” ከሚል ጋር ተያይዞ የመጣ እንደሆነ ይገልፃሉ። ለየት ያለና ዘና የሚያደርግ፣ መዝገበ ቃላት ይመስላል።)
ምንጭ Reason for Ethiopia

EBC New TV Series Yebet Sira (የቤት ስራ) – Episode 01

$
0
0

EBC New TV Series Yebet Sira (የቤት ስራ) – Episode 01….Yebet Sira (የቤት ስራ) – Episode 01…….EBC New TV Series Yebet Sira (የቤት ስራ) – Episode 01

★አብርሀ ደስታ ዋጋውን እስከ ሞት የተመነለትን ነፃነት በኢትዮጵያ አብቦ እና ፈክቶ አየው ዘንድ እናፍቃለሁ★ (ሮቤል አያሌው )

$
0
0

ዛሬ እንደወትሮዬ አብርሀ ደስታን ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ አምርቼ ነበር። ታዲያ አብርሀን ሆነ መሰሎቹን ለመጠየቅ እንዲህ በቀላሉ የሚቻል አይደለም። በጥብቅ ከሚጠበቀው ቃሊቲ ውስጥ ለመጠየቅ የሚፈቀደው ከ 6:00 – 6:30 ያለችን 30 ደቂቃ ብቻ ስትሆን እሱም በር ላይ ቆመው የአይንህ ቀለም አላማረንም እያሉ የሚመልሱ ደህንነቶችን ማለፍ ከተቻለ ብቻ ነው። እናም ከብዙ ንትርኮች(እምባ ቀረሽ ልመና) በኃላ የያዝኩትን የፆም መፍቻ ምግብ ይዤ ወደ ውስጥ ዘለኩ።

4vb
ከዛም ከአብርሀ ጋር በሽቦ በተከለለው መጠየቂያ ጣታችንን አሾልከን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ በቀጥታ ስለ ፍርድ ቤቱ ውሳኔና ስለ ቀጣይ ሁኔታ ማውራት ጀመርን። አብርሀ ተፈቶ ከሚተነፍሰው አየር በላይ እየታየው ያለው – ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ነው። እኔም ከዚህ በኋላ ለመውጣት ስንት ጊዜ እንደሚቀረው ፍርድ ቤቱን ደፍራቹሀል የተባለውን የፍርድ ውሳኔ በማንሳት በጥያቄ መልክ አስከተልኩ። እሱም “አስቀድሞ በተከሰስንበት ፍርድ ነፃ ናችሁ ስለተባልን ፍርድ ቤቱን በመድፈር በሚል የተላለፈብን የቅጣት ውሳኔ እስከዛሬ በእስር ላይ በቆየንበት ጊዜ የሚጣፋ ይሆናል። ይህም በእኔ የተላለፈው የ 16 ወር የቅጣት ጊዜ አመክሮ የማይታሰብ ከሆነ ጥቅምት 24 የእስር ጊዜዬን ጨርሼ የምፈታ ሲሆን አመክሮዬን በህጉ መሰረት ተፈፃሚ ከተደረገ በሚቀጥሉት ቀናት የምወጣ ይሆናል። የሽዋስ እና ዳንኤል ደግሞ የ14 ወር ጊዜ የተፈረደባቸው ስለሆነ በህጉ መሰረት አመክሮ የሚታሰብላቸው ከሆነ በሚቀጥሉት ቀናት የሚፈቱ ይሆናል፤ ይህን መብት ከከለከሏቸው ግን ነሀሴ 30 የሚፈቱ ይሆናል።” ሲል ተስፋውን ገለፀልኝ።” እኔም ሲቪል የለበሰው አዛዥ(ደህንነት) ዛሬ የመጨረሻ እንደምጠይቀውና ከዚህ በኋላ መጠየቅ እንደማልችል ስለነገረኝ የአብርሀን ከእስር የመውጣት ዜና በጉጉት እየጠበኩ እገኛለሁ።
በመጨረሻም
★አብርሀ ደስታ ዋጋውን እስከ ሞት የተመነለትን ነፃነት በኢትዮጵያ አብቦ እና ፈክቶ አየው ዘንድ እናፍቃለሁ★ (ሮቤል አያሌው )

Viewing all 3774 articles
Browse latest View live