የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ቸሎት በእነ ኦሞት አግዋ ሶስት ተከሳሾች ባሉበት መዘግብ ለዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2008 ዓ.ም የተቀጠረው ተከሳሾች ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ እና አቃቤ ህግ የሰጠውን ምላሽ መርምሮ ብይን ለመስጠት ቢሆንም ችሎቱን በስብሳቢነት የመሩት የመሃል ዳኛ ታርቀኝ አማረ “መዝገቡ ከሌሎች መዝገቦች ጋር ተደራርቦ’ ተረስቶ አልተሰራም፡፡ ብይን ለዛሬ አለደረሰልንም ” በማለት ተለዋጭ ቀጠሮ ለጥር 2 ቀን 2008ዓ.ም ሰጥተዋል፡፡
በዕለቱ ቸሎት ሶስተኛ ተከሳሽ ጀማል ኡመር ማዕከላዊ ምርመራ ላይ በነበሩበት ወቅት የህክምና ቀጠሮ በፖሊስ ሆሰፒታል ለመስከርም ወር ተቀጥሮላቸው የነበረ ቢሆነም የቀሊንጦ ማርሚያ ቤት አስተዳደር ወደ ፖሊስ ሆሰፒታል ሄደው አነዲታከሙ ፈቃድ ሊሰጣቸው አነዳልቻለ ለፍርድ ቤቱ በቃል አቤቱታ ያመለከቱ ሲሆን የመሃል ዳኛው በቅድሚያ አቤቱታቸውን ለቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ማቅረባቸውነ ጠይቀዋቸዋል፡፡ ተከሳሹ ጀማል ኡመር በተደጋጋሚ ማረሚያ ቤቱን እነደጠየቁና ምላሽ እንዳላገኙ ተናገረዋል፡፡
የመሃል ዳኛው ታርቀኝ አማረ “ፍርድ ቤቱ እከሌ እዚህ ሆስፒታል እከሌ እዚህ ሆሰፒታል ይሂድ ብሎ ማረሚያ ቤቱን የማዘዝ ሰልጣን የለውም፡፡ ማረሚያ ቤቱ ሆሰፒታል አልወስድም ካለ ብቻ ለኛ ይንገሩን፡፡ እርስዎ መጀመሪያ ማረሚያ ቤቱን ይጠይቁና ከተከለከሉ ፍርድ ቤቱ ያን ጊዜ ያዛል” በለው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
Ethiopia Human Rights Project
·
↧
በነ ኦሞት አግዋ የተከሳሸ መዘገብ የዋለው ችሎት ብይን ሳይሰማ በድጋሚ ተቀጠረ፡፡
↧