Quantcast
Channel: Kalkidantube
Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

ኮሎኔል ተስፋዬ ወልደሥላሴ ፣ስለ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

$
0
0

11304508_1456693524644722_1135012595_n
ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር በጣም እንተዋወቃልን ከሀይለስላሴ ጊዜ ጀምሮ፡፡ ጠንካራ ሰው ነው፡፡ ሃገር ወዳድ ነው፡፡ ለማንም መሪ አያጎበድድም፡፡ ለማንም የሚያጎነብስ አይደለም፡፡ ለውጡ ሲመጣ ፣ መስፍን እነ አጥናፉ እነ መንግስቱን በቀና መንፈስ ቀረባቸው፡፡ አንዳንድ ሃሳቦችን ይሰጣቸው ነበር፡፡ ይወያያል፡፡ የመርማሪ ኮሚሽኑን ሚና ከሕግ አንፃር ነበር የሚያየው፡፡ ከዚህ የተለየ አቋም ይይዛል ብዬ አላምንም፡፡ በሕጋዊ መንገድ ጉዳያቸው ታይቶ ለፍርድ ይቅረቡ ከሚለው ውጪ ሌላ ይሆናል ብዬ አላስብም፡፡ ቀስ በቀስ የሶሻሊዝሙ ጉዳይ እየጠነከረ ሲመጣ እሱም ከነሱ በሃሳብ እየተለየ መጣ፡፡ ከዚያ በውሃላ እየራቃቸው ሄደ፡፡ አመራሩን እየራቀ መጣ፡፡
መስፍን በብዙ ድርጊቱ፣ በብዙ አሠራር ፣ በኢትዮጵያነቱ ፣ ለሃገሩ የሚያስብ ነው፡፡ አንድ ጊዜ ሲያጫውተኝ ፣ ፕሬዝዳንት መንግስቱ አንድ ቀን ከቤት አስጠሩኝና አነጋገሩኝ፡፡ ያሉኝ ምንድነው <<ደብረዘይት መንገድ ላይ አንዲት ቅጠል ተሸክመው የሚሄዱ አሮጊትን መኪና ገጭቷቸው ጠፋ፡፡ ስለዚህ የኝህን ሴት ደም መበቀል አለብን፡፡ ይሄን እንድታደርግልኝ እፈልጋለው>> አሉኝ፡፡በኋላ እደጅ ወጥቼ <<ኢትዮጵያ ለድሆቿ የሚያስብ መራ አሁን አገኘች>>አልኩኝ፡፡ <<ይሄንንም ነገር እንደራሴ ጉዳይ ወስጄ ከፖሊስም ከምንሞ ብዬ ገጪውን ማግኘት አለብኝ ብዬ ተነሳሁ፡፡ በመንግሥቴ በጣም ደስ አለኝ፡፡ያንን ጉዳይ አጣራሁ፡፡ ጉዳዩን ከሚመለከተው ፖሊስ ጋር አገናኘሁና ፖሊስ ደረሰበት፡፡ ሰውዬውን ፍርድ ቤት አቅርበው ቀጡት እና በዚህ ደስ አለኝ፡፡ በኋላ ግን እየቆዩ ፣ እየቆዩ ከተነሱበት ዓላማ እየሸሹ ሲመጡ ራቅሁ>> ብሎ አጫወተኝ፡፡ አሁንም ያኔ በመንግስቱ ሀይለማርያም ዙርያ የነበሩ እንዚ ሶሻሊዝምን ተምረናል የሚሉ ፣ ኮሚንዝምን እናውቃለን የሚሉ ሁሉ ፕሮፌሰር መስፍን ኮሚኒስት ሳይሆን ፣ ዲሞክራት ነው የሚል ታርጋ ለጠፋበት፡፡
ደግሞ አንድ ቀን እንደዚሁ ፕሬዝዳንቱ አስጠሩትና አነጋገሩት፡፡ እኔ አልነበርኩም፡፡ እነሱ ሲነጋገሩ አጠገባቸው ሆነው የተባባሉትን የሰማው ሻምበል ፣ <<እኝህ የርስዎ ወዳጅ ፕሮፌሰር መስፍን አበዱ ልበል? ፕሬዝዳንቱ ጋር ቀርበው ፣ ይሄንን አድርገን ፣ ይሄንን ፈጥረን>>ሲሏቸው ፣ <<መቼም ጏድ መንግስቱ ፣ እርሶዎ እኮ በመሪነትዎ ለወደፊት ለታሪክም ጭምር ማሰብ ይገባዎታል፡፡ ታራክ ደግሞ ዛሬ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ለይ ስለርስዎ የሚጻፈው አይመስልዎት፡፡ በዚህ ላይ በጣም ፣ በጣም ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል>> ብለው ደፍረው ተናገሯቸው፡፡ መንግስቱም ቅር አላቸውና ወጥተው ሄዱ አለኝ፡፡ እኔም መስፍን ወዳጄ ስለሆነ አስጠራሁትና << እንዴት ነው አንተ እንደዚህ ብለህ የተናገርከው?>> አልኩት እሱም << የነተናገርኩት አንተ ጋር ይደርሳል ብዬ አላሰብኩም፡፡ ግን እኮ ያልኩት ትክክል ነው፡፡ አንተ እንዴት አየኸው?>> አለኝ፡፡ << አይደለም ሰውዬውን በለሰለሰ ሁኔታ ብትያዘቸው ይሻላል እንጂ እንዲህ ጠንከር ስትል ያገሉሃል፡፡ ሃሳብህን እንኳን እንዲህ ነው ብለህ ለማለት ዕድል አታገኝም>> አልኩት፡፡ ስለዚህ መስፍን እንዲህ ነው ፣ እንዲህ ነው የሚባለው ነገር ከጥላቻ ይመስለኛል እንጂ እሱ በንጉሠ ጊዜ የነበረው አቋም ፣ በደርግ ጊዜ የነበረው አቋም ፣ አሁንም በኢሐዴግ ያው ነው፡፡ አልተለወጠም፡፡ ኢትዮጵያ ፣ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ አላት ብዬ የምለው ሰው ነው፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

Trending Articles