በዛሬው እለት ታህሳስ 21ቀን 2008 ዓም የመምህር ግርማን ክስ ለመመልከት ቀጠሮ ይዞ የነበረው
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ፍርድ ቤት ፖሊስ በተሰጠው የ31ቀን ግዜ ቀጠሮ ምንም አይነት ማስረጃ ሊያቀርብ ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ የ100 ሺህ ብር ዋስ ጠርተው እንዲፈቱ ውሳኔ አሳልፏል።
ፖሊስ ” ዛሬ ወደ አድዋ ጸበል ስትጠመቅ የሞተችውን ግለሰብ አስክሬን ለመመርመር ባለሞያ ልከናል”የሚል መልስ በመሰጠት የግዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲል ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ እንዳደረገው ምንጮች ለቃልኪዳን ቲዩብ ገልጸዋል።
ፍርድ ቤቱ ዋስትና ከመሰጠቱ በፊት መምህር ግርማ የሚሉት ነገር እንዳላቸው ሲጠይቃቸው ፤ ” በሦስት ሐሰተኛ ክሶች ከሁለት ወር በላይ ወገኔን በማገልገሌ ፍትህ አጥቼ እየተጉላላሁ እገኛለሁ።የሦስት ልጆች አባት እና የቤተሰብ አስተዳዳሪ ነኝ።” በማለት የተናገሩ ሲሆን።
የመምህር ግርማ ቤተሰቦች ፍርድ ቤት የፈቀደውን የዋስትና ገንዘብ ቢከፍሉም ፖሊስ ይግባኝ በመጠየቁ ፍርድ ቤት ለታህሳስ 25 ቀን 2008 ከጠዋቱ 3 ሰአት ቀጠሮ ይዟል።
↧
መምህር ግርማ ወንድሙ በመቶ ሺህ ብር ዋስትና እንዲወጡ ፍርድ ቤት ቢወስንም ፖሊስ ይግባኝ ጠየቀ።
↧