የኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት የፈረጃቸው የአርበኞች ግንቦት7 ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ አገር ቤት ተመልሰው ባለፈው ግንቦት ወር ተካሂዶ በነበረው ምርጫ እንዲሳተፉ ሸምግልና ተልከው እንደነበር ሚስ አና ጎሜዝ ተናገሩ።
የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባል እና የኢትዮጵያ የምርጫ 97 የህብረቱ የምርጫ ታዛቢ ልኡካን መሪ ሚስ አና ጎሜዝ ባለፈው ሳምንት የአውሮፓ ፓርላማ አዘጋጅቶት በነበረው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተጋበዙበት ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት ” መንግስት በአንድ በኩል ፕ/ር ብርሃኑን ሽብረተኛ ይላቸዋል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ወደ አገር ተመልሶ በምርጫው እንዲሳተፍ መልእክት እንዳስተላልፍላቸው ጠይቀውኝ ነበር” ያሉት አና ጎሜዝ፣ መልእከቱን ለፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ማድረሳቸውን ፕሮፌሰሩ መሰረታዊ የሚባሉት ጥያቄዎች የፕሬስ ነጻነት፣የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣ገለልተኛ ምርጫ ቦርድ ይቋቋም የሚሉ ጥያቄዎች ከተሟሉ በምርጫው ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን መልስ እንደሰጧቸው ተናግረዋል።
ይሁን እንጅ የኢትዮጵያ መንግስት መመለስ አለባቸው የተባሉት መሰረታዊ ጥያቄዎች ባለመመለሳቸው ኢህዴግ ምርጫውን 100 በመቶ አሸንፍኩ በማለት አስደምሞናል ብለዋል።
ጥያቄው መቼ እንደቀረበላቸው የገለጹት ሚስ አና ጎሜዝ የአፍሪካና ካረቢያን አገራት የፓርላማ አባላት ስብሰባ ለመካፈል ወደ አዲስ አበባ ባቀኑበት ወቅት መሆኑን ገልጸዋል።
↧
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2007ቱን ምርጫ እንዲወዳደሩ የኢትዮጵያ መንግስት ሽምግልና ልኳቸው እንደነበር ሚስ አና ጎሜዝ ተናገሩ።
↧