Quantcast
Channel: Kalkidantube
Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

ኦሮሚያ ክልል የተማሪው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሏል፤ የፊንጫ ሰኳር ፋብሪካ ሰራተኞች ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል::

$
0
0

poi123
የኦሮሞ ተማሪዎች ቁጣ በመላው ኦሮሚያ በሁሉም ከተሞችና የገጠር ከተሞች ተቀጣጥሏል። “የመሳርያ አፈሙዝ መብታችንን ከመጠየቅ አያግደንም”፣ “የተማሪዎች ጥያቄ የኦሮሞ ገበሬዎች ጥያቄ ነው” ፣”ማስተር ፕላናችሁን እምቢ ብለናል” የሚሉ ተማሪዎች በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ እያቀረቡ ነው።መንግስት የፌደራል እና የአጋዚ ጦርን የኦሮሚያ ፖሊስ ልብስ አልብሶ ተማሪው ላይ እየተኮሰ ነው።
ተቃውሞው በወሊሶ ዩንቨርስቲ ፣ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና በአምቦ አቅራቢያ ኦሎንኮሚ ከተማ በምእራብ ሸዋ ጌዶ ፣ ሙገር ፣አደአ በርጋ ፣ ሰላሌ፣ሻሸመኔ ተማሪዎች ሕዝቡ እና የሃገር ሽማግሌዎች ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል:: በተማሪዎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ ያስቆጣቸው የፍንጫ ሰኳር ሰራተኞች የተቃውሞውን ትግል የተቀላቀሉ ሲሆን በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የኦሮሚያ የመንግስት ሰራተኞች ድምጽ አልባ ተቃውሞ እያሰሙ ነው።
ትላንት በመንግስት ወታደሮች ተደብድበው የተበተኑት የአዳማ ዮኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬ በድጋሚ ተቃውሞቸውን እያሰሙ ነው ። ፣ከፍተኛ የተቃውሞ ውጥረት ውስጥ ያለው አርሲ ዩንቨርስቲ አሰላ በመንግስት ወታደሮች ቁጥጥር ስር ውሏል::
በየቦታው ተማሪዎች ተገድለዋል በተማሪዎች እንቅስቃሴ ዙርያ መንግስት ከማረጋጋት ይልቅ የሀይል አማራጭን መርጧል።ትምህርት ቤቶች በወታደሮች ተከበው ጦር ቀጠና መስለዋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774