Quantcast
Channel: Kalkidantube
Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

ድንቄም “የኦሮሞ አባት” –ስለ የተቀናጀ ማስተር ፕላኑ አንዳንድ ነገሮች( ሰለሞን ስዩም) ——–

$
0
0

ሪፖርተር ጋዜጣ ከአዲስ አበባ መስተዳድር የከተማ ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃየሎም ጣውዬ ጋር ያደረገው ቃለ-ምልልስ የሰሞኑን አየር አግሏል (እኔንም ከሳምንታት ህመሜ እንደመባነን አድርጎኛል)፡፡ የቢሮ ኃላፊው የአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን በቀጣዮቹ ወራት እንደሚተገበር ገልጧል፡፡ (በነገራችን ላይ የኦሮሚያ ክልል ህገ-መንግስት እና በክልሉ የሚገኙ ቢሮዎች ከተማዋን “ፊንፊኔ/Fiinefiinnee” እያሉ ሲጠሯት፣ ፌዴራል መንግስቱና ከተማዋ ራሷ”አዲስ አበባ” እያሉ እንዴት ይግባባሉ፤ ድሪባ ኩማ ራሱ ኃየሎም ጋር ሲሆን “አዲስ አበባ” ሲል ለጨፌ ስብሰባ ሲሄድ ደግሞ “ፊንፊኔ” ይላል፡፡)

Addis Ababa, Ethiopia kalkidan
ለመሆኑ የዚህ ማስተር ፕላን ችግር ምንድነው ከተባለ መልሱ ጥናት ይጠይቃል የሚል ነው፡፡ ጥናት የማይጠይቀው ግን ከተለመደው የህወሓት መሰሪ አካሄድ አንፃር ለተባለው ጉዳይ ይውላል ብሎ መጠበቁ ሞኝነት መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ብዙ ግድፈቶችን ማንሳት ይቻላል፡፡
አዲስ አበባ በዋናነት ወደ ምስራቅ፣ ምዕራብና ደቡብ በእጅጉ ተለጥጣለች፤ ይህ በዘመናዊ የከተማ ዕድገት እሳቤ አይመከርም፡፡ የሆነ ሆኖ ግን ስትለጠጥ ከምስረታዋ ጀምሮ በቱለማ ስር ያሉትን የገላንና ጉለሌ የኦሮሞ ጎሳዎችን በማፈናቀል ነው፡፡ መሰረቷ የሆነው ፍልውሃ፣ ጎሳዎቹ “ሆራ”(የከብቶች ውሃ ማጠጫ) ሲሆን የአራት ኪሎው ቤተ-ፖለቲካ ደግሞ የገላን መሪ ቱፋ ሙና ግቢ ነበር፡፡ አራዳ ለኦሮሞ ልዩ ቦታ ያለው “ድሬ ብርብርሳ” ነው፡፡ (በነገራችን ላይ ኦሮሞ ከ12ኛው መቶ ክ/ዘ በፊት በዚህ ቦታ እንደነበር አስተማማኝ መረጃ እየተገኘ ነው፡፡) አሳዛኙ ነገር ከ100 ዓመታት በፊት የጀመረው ይህ ማፈናቀል ዛሬ ድረስ አልቆመም፡፡ የአዲስ አበባን መስፋፋት ልዩ የሚያደርገው የተስፋፋችበትን አከባቢ ነዋሪ ያለማቀፏ ነው፡፡ እንደዚህ አይነቱ ሂደት “የዘውግ ማጥራት” (Ethnic Cleansing) በሚል የፖለቲካ ንድፈ-ኃሊዮ ይታያል፡፡
ከተማ መስፋፋት አለበት፤ ነገር ግን ነባሩ ነዋሪ ተጠቃሚ እንዲሆን ከከተማው ጋር ማደግ ነበረበት፤ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚሰራው ግን ሙሉ በሙሉ አንዱን በሌላ መተካት (Replacement)ነው፤ ከተማ የደረሰበት ነዋሪ ተሰዳጅ፣ ለማኝ፣ ከትምህርቱ የሚያቋርጥ …ሲሆን መጤው ግን ይጠቀማል፡፡ በመርህ ደረጃ ከተማ ወደ ጎን ሲለጠጥ ሰዎቹን ወደ ውስጥ መሳብ አለበት፤ ብርሃኑ መገርሳ የተባለ ሰው (በ “OMN” ከተናገረው) የመመረቃ ፅሁፉን በዚህ ርዕስ ላይ ሲሰራ የገጠመው ነገር ተመሳሳይ ነበር፤ ከተማው የደረሰባቸውን ሰዎች አግኝቶ ማነጋገር አልቻለም፤ ምክንያቱም ጠፍተዋል፡፡ ይኑሩ ይሙቱ አይታወቅም፡፡
አንድ በጄ የሚገኝ ሰነድ ወሽንግተን ዲሲ እንዴት እንደተስፋፋች ሲገልፅ “አሜሪካኖች በቀይ ህንዶች ላይ የሆነውን ድጋሚ ለማያት አልፈቀዱም፤ በዋሺንግተን ዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ነዋሪ የነበሩ ዜጎች የከተማዋን መስፋፋት እንደ ዕድል ነበር የቆጠሩት” ይላል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከማንም በተሸለ መብታቸው ተከብሮ ስለ ተከናወነ ነበር፡፡ እዚህ ግን ልማቱ ሰዋዊ ሳይሆን “ተጋሩ”አዊ ነው፡፡ መሬት በመሸጥ መክበር፡፡ ተጋሩ የሚንጠባጠበውን ደግሞ የኦህዴድ ጥንብ አንሳ አለለት፡፡
ወይ መሬት! “መሬት የግል ከሆነ ገበሬው ሸጦ ይሰደዳል” ያለው ገዥም፣ ሻጭም፣ አሳዳጅም ሲሆን ይነዳል፡፡
“Koottu yaa dachii too
Dachii haadha margaa
Irri kee midhaani
Jali kee bishaani
Yookan tiyya taataa
Yookan siif nanyaataa” ከሚለው ጌረርሳ “Yookan siif nanyaataa” (መሬት ላንቺ ሲሉ በሉኝ) የሚለው ተፈፀመ፡፡
በንድ ነገር ላይ እንስማማ፤ ከተሞች ይደጉ፤ ነገር ግን “ልማት” ይሆን ዘንድ ባለቤቱ መፍቀድ አለበት፤ የአከባቢው ነዋሪ ሲፈልግ ልማቱን አልፈልግም ማለት ይችላል፡፡ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉት ደግሞ፣ በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 49/5 መሰረት፣ እንኳን መፈናቀል ልዩ ጥቅም በተገባቸው ነበር፡፡ ነገሩ በትልቀት ከታየ፣ “መንግስት” ህዝቡ እንዲመክርበት ያለ መፍቀዱ፣ የህገ መንግስቱን አንቀፅ 39/3፣ 49/5፣ 38/1/ሀ ኢህአዴግ ቀን በቀን ከሚደረምሳቸው አንቀፆች ጥቂቶቹ መሆናቸውን እንረዳለን፡፡
ሌላው ጉዳይ እንኳን የአከባቢው ህዝብ ቀርቶ መላ ኦሮሚያ አከባቢዎች ከዚህ ሀሳብ በተቃራኒ ነበር የቆሙት፡፡ ተቃውሞ አለርጂው የሆነው ኢህአዴግ ግን ብዙ ሰው በእስር ቤት አጉሯል ፤ ከዩኒቨርሲቲ አዱኛ ኬሶ፣ ቶፊቅ ረሺድ፣ ደራርቱ፣ ሌንጂሳ አለማዮ፣ አብዲ ከማል፣ መገርሳ ወርቁ፣ ቢሊሱማ ዳመና… መጥቀስ ይቻላል፡፡ አበበ ኡርጌሳ የማዕከላዊን ሰቆቃ መቋቋም አቅቶት አስከ ወደዲያኛው አሸልቧል፡፡ በወለጋ ቤጊ የ11 ዓመቱ ሀተኡ፣ በአምቦ (36 ሰዎች)… በጥይት ተደብድበው ተገለዋል፡፡ የሚገርመው ደግሞ በዚህ ተቃውሞ ቦቅቧቆቹ ኦህዲዶችም ያለወትሯቸው ተሳትፈዋል፡፡ አመራሮች ሳይቀሩ፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ የተለየ መግባባት ሳይፈጠር ይተገበራል ማለት በሃልዮ መነፅር ከታየ “የፖለቲካ እብሪት” ነው፡፡ ለዚህ ምስክር ጥሩ ብንባል “የአባ” አባይ ፀሀዬን ድንፋታ እንጠራለን፡፡ (አንድ አንድ ሰዎች ህወሓት ተዳከመች ይላሉ፤ ይህ ኃይልን በፖለቲካ ስልጣን ብቻ ከማት የመጣ ነው፤ ለዚያም ቢሆን ባያንሳቸውም (ጌታቸው አሰፋ እና ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ ብቻ ይበቃሉ) ከንግዲህ ግን ኃይል ኢኮኖሚ ነው፡፡ ኢኮኖሚ ደግሞ ለነሱ አይነገርም፡፡
አዲስ አበባ የኦሮሚያ ገበሬን በ17 ብር በካሬ ታፈናቅልና ለራሷ ከ300,000 በላይ በካሬ ትሻጣለች፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ያለው የተጋሩ ድብቅ የማፈያ “መንግስት” የሚሰራውን ጊዜ ከሰጠኝ (የማፊያ ቡድኑ) በክፍል ሁለት እመለስበታለሁ፡፡
አዲስ አበባ ውለታ አታውቅም ፤ አንዳንዱን በስጋው ትገለዋለች፤ አንዳንዱን በመንፈስ፡፡ ከሱሉልታ በጎጃም በር አህያ እያነዱ ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ሰዎች አቋራጭ መንገድ ነበራቸው፤ ዛሬ ያለምንም ርህራሄ “ለመለስ ዜናዊ ፓርክ” ተብሎ በመታጠሩ ብዙ ርቀት ተጨምሮባቸው ከመኪና ጋር ለመጋፋት ተገደዋል፡፡ ከርቀቱ መጨመርና ከመኪናው ግፊያ በበለጠ ግን በሱ መሬት መኪና በገዘው ማፊያ “ቦታም ጋላ” ተብሎ ስሳደብ እጅጉን ያመዋል፤ ድንቄም “የኦሮሞ አባት”
አዲስ አበባ-የደም መሬት
አዲስ አበባ- አኬልዳማ
“…Yookan tiyya taataa
Yookan siif nanyaataa”


Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

Trending Articles