አብዛኛው የትግራይ የፌስቡክ አክትቪስቶች፣ ወጣቶችና ሙሁራን የህወሐት አባላት፣ ሌሎች ለውጥ ፈላጊ አክትቪስቶችና ሌሎች ፖለቲከኞች በጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ።
የአርከበ በድምፅ በጉባኤው መሳተፍ ለብዙዎች የአዲስ አበባው አንጃ ወደ አሸናፊነት የተጠጋ ቢመስላቸውም ጉዳዩ ሌላ ነው።
አርከበ ተመልሶ የማይወዳደር መሆኑ ስላረጋገጡ የትግራዩ አንጃም እንዲሳተፍ በአንድ ለ አምስት ኔትወርክ ታስረው የመጡት የወረዳ ተሳታፊዎች(ማንበብና መፃፍ የማይችሉ የሚገኙባቸው ሴቶችና ገበሬዎች የሚገኙባቸው የአባይ ወልዱ ታማኞች ) እንዲፈቅዱለት አድርገዋል።
እንዲሳተፍ የተቀሰቀሰው ” አርከበ የመጣው ለሊቀ መንበርነት ሳይሆን በባቡርና ኢንዳስትሪ ከፍተኛ ስራ እንዲሰራ ነው። ስለዚ ቢሳተፍ ችግር የለውም ” የሚል ተነግሮሯቸው ነው።
“አባይ ደራ” የሚል የበረሃ ስሙ በመጥራት ” ከመለስ ሞት በኃላ ድርጅቱ አጋጥሞት የነበረው ከፍተኛ ችግር ያለ አባይ ደራ ምርጥ መሪነት ድርጅታችን ለመበታተን ይዳርጋት ነበር ” የሚል ፕሮፖጋንዳ ተምረው አጥብቀው በመያዝ አሁንም ሌላ ኣማራጭ እንደሌለ አምነው ለማስፈፀም ተዘጋጅተዋል።
ወፍ የለም “አባይ ደራ ” የአንድ ለ አምስት ኔትወርክ ሲቆጣጠሩ የቴሌው ኔትወርክ ደግሞ ዶክተር ደብረፅዮን በእጃቸው ይገኛል።
አባይ ወልዱ የቴሌው ኔትወርክ ለመቆጣጠር ሞባይል ስልክ ወደ አዳራሽ እንዳይ ገባ አድርገዋል።
እነ ዶክተር ደብረፅዮን ደግሞ የአንድ ለ አምስት ኔትወርክ እንዳይሰራ መበተን ይጠበቅባቸዋል።
ለውጥ ……………… የምትጠብቁ የዋሆች እርማቹ አውጡ።
በስብሰባው አንድ ተሳታፊ ህዝቡ ክፉኛ ተቀይሞናል፣ የመረጠንም ዕሬት ዕሬት እያለው ነው። ስለዚ ለውጥ የህልውናችን ጉዳይ ነው። አለበለዚያ ጥፋት ቅርብናት በማለት የተናገረው ደማቅ ጭብጨባ አስገኝቶለታል።
ስብሰባው ከተያዘለት ግዜ በላይ እንደሚፈጅ ታውቋል።
የመቐለ ከሐወልቲ እስከ ኡክሱም ሆቴል ያሉ ጎዳናዎች በቖልዑ አሸንዳ ምትክ ብሬን የጫኑ ፓትሮል የፌደራል ፖሊስና የክልል ልዩ ሃይል እየጠበቁ ነው።