ህወሀት ቴዲ አፍሮን ከልክ በላይ እየገፋው ነው:: ለቴዲ የህወሀት ኢትዮጵያ አላስቀምጥ ብላዋለች:: ምናልባትም ቴዲ ከሀገር ተሰደደ የሚል መራር ዜና ልንሰማ የምንችልበት ጊዜ እየቀረበ እንደሆነ ይሰማኛል:: በግሌ በተለይ ሰሞኑን የሚደርሱኝ መረጃዎች የህወሀትን የዕብሪት ለከት ማጣት የሚያሳዩ ቴዲንም ከሚወደው ህዝብና ከሚሳሳላት ሀገሩ እንዲለያይ የሚገፋፉ ናቸው::
Image may be NSFW.
Clik here to view.
ቴዲ መሰደድ እንደማይፈልግ የትኛውንም በደል ተቋቁሞ በሀገሩ መኖር ለምርጫም የማይቀርብ ጉዳይ እንደሆነ ባውቅም ትዕግስትም ልክና ድንበር አለውና የሰሞኑ ግፊትና ግፍትሪያ ከመራር ውሳኔ ሊያደርሰው እንደሚችል አምኜአለሁ::
ቴዲ ከእናቱ ቤት መሀል አዲስ አበባ እሱ ወደ ሚኖርበት ሲ ኤም ሲ በየጊዜው ሲመላለስ በደህንነቶች ታጅቦ: በመንገድ ላይ እያስቆሙ መከራውን አሳይተው በሚፈትሹት የህወሀት ሰዎች ተንገላቶ መሆኑ አስገራሚ ነው:: ቤቱ በደህንነቶች እጅ ላይ ወድቋል:: ዙሪያውን ይቆጣጠሩታል:: እንዳሻቸው እየጠሩ ያስፈራሩታል:: ከተቃዋሚዎች ጋር ትገናኛለህ በሚል ክብረ ነክ ምርመራ ያደርጉበታል:: በቅርቡ ባለቤቱ ታማ ወደ ኬኒያ ይዟት ሊሄድ ሲል መንቀሳቀስ የጀመረን አውሮፕላን እንዲመለስ አድርገው እንደ ወንጀለኛ በተሳፋሪ ፊት እየገፈተሩ ወስደውታል:: በተደጋጋሚ የውጭ ጉዞዎቹ እንዲሰረዙ አድርገዋል:: በርካታ ሌሎች ጥቃቶችን ፈጽመውበታል:: ለፊታችን አዲስ ዓመት በላፍቶ ያዘጋጀው ኮንሰርትም ሊሰረዝ እንደሆነ ከውስጥ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል:: በአዲስ አበባ ለህወሀት የሚጮሁ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የላፍቶው ኮንሰርት የሚሰረዘው በስፖንሰር እጦት ነው በሚል ቢያራግቡም እውነታው ግን የምንመርጥልህን እንጂ የመረጥካቸውን ዘፈኖች አታቀርብም ብለው ጣልቃ በገቡ የደህንነት ሰዎች ግፊት ነው::
ቴዲን ህወሀት ከሀገር ገፍትሮ ሊያስወጣው እየሞከረ ነው:: መንፈሰ ጠንካራ የሆነው ቴዲ እስከአሁን በትዕግስት እየመከተ ነው:: ሰው ነውና መንግስትን የሚያክል ሃይል ተነስቶበት ብቻውን ይመክታል ማለት አይቻልም:: ከጎኑ መቆም ግድ ይላል:: ህወሀት ቴዲ ላይ አይደለም ሰይፍ የመዘዘው:: ትውልዱ ላይ ነው:: ኢትዮጵያዊነት ላይ ነው::