የአዲስ አበባና የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ንድፍ ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ፣ በመላው ኦሮሚያ ከሕዳር ወር ጀምሮ የተቀጣጠለው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን ቪኦኤ ዘግቧል። በመሰላ ከተማ አባድር በተባለ ቦታ የአንድ ተማሪ አስክሬን ጉድጓድ ወድቆ መገኘቱን እንዲሁም አንድ የሐሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ከፎቅ ላይ ወድቆ ሕይወቱ ማለፉን የዘገበው ቪኦኤ በምን ምክንያት ከፎቁ ላይ እንደወደቀ አለማወቃቸውን የገለጹ የዐይን እማኞች ከወደቀበት አንስተው ሆስፒታል እንደወሰዱት እዚያም እጃቸው ላይ ሕይወቱ እንዳለፈ ተናግረዋል ብሏል፡፡የቪኦኤን ሙሉ ዘገባ ጽዮን ግርማ አቅርባዋለች አድምጡት።
↧