Quantcast
Channel: Kalkidantube
Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

በኦሮምያ ጉዳይ የሲቪከስና የአምነስቲ መግለጫና አቋም-VOA Amharic

$
0
0

የኢትዮጵያ የልማትና ዓለምአቀፍ አጋሮች ኦሮምያ ውስጥ ተገድለዋል ያሏቸውን ከ140 በላይ ሰዎች ጉዳይ በቅርበት እንዲፈትሹ ሲቪከስ ተብሎ የሚጠራው የዜጎች ተሣትፎ ዓለምአቀፍ ጥምረት ጥሪ አሰምቷል፡፡
ሲቪከስ የዛሬ 23 ዓመት የተመሠረተ ዓለምአቀፍ ጥምረት ነው፡፡
ሲቪከስ በመላው ዓለም የዜጎችን የተግባር እንቅስቃሴና ሲቪሉን ማኅበረሰብ ለማጠናከር በሚል ዓላማ የተመሠረተ፤ ዛሬ በ145 ሃገሮች ውስጥ አባላት ያሉት፤ ዋና ፅሕፈት ቤቱ ጆሃንስበርግ – ደቡብ አፍሪካ የሆነና ለንደን፣ ጄኔቫና ኒውዮርክ ቢሮዎችን ከፍቶ እየሠራ ያለ ተቋም ነው፡፡
የሲቪከስ የምሥራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ የመብቶች ዘብ ወይም “ለዘቦች ዘብ ቁሙ” በሚል የተሰየመው ፕሮጀክት እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሚባለው ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን ሐሙስ፤ ጥር 15/2016 ዓ.ም ባወጡት መግለጫ ለኢትዮጵያ የልማትና ዓለምአቀፍ አጋሮች አቤቱታ አሰምተዋል፡፡
ሲቪከስና አምነስቲ ኢንተርናሽናል በዌብሳይታቸው ላይ ባወጡት ጥሪ ኢትዮጵያ ውስጥ ከህዳር አንስቶ ተገድለዋል ያሏቸው ከ140 ሰዎች በላይ ጉዳይ በትኩረት እንዲይዙ ነው የጠየቁት፡፡የኦሮሚያ አለመረጋጋት የተጫረው ኅዳር 2/2008 ዓ.ም ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምዕራብ በሚገኝ የኦሮምያ ክልል ሥፍራ የአንድ ትምህርት ቤትና ደን ይዞታዎች ለግል ባለሃብት መሰጠታቸውን ተቃውሞ በማሰማት የአካባቢው ሰዎች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት እንደነበር የሲቪከስና የአምነስቲው መግለጫ አስታውሶ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ተቃውሞዎቹ በይዘትም በስፋትም እያደጉ መምጣታቸውን ተናግሯል፡፡
ተቃዋሚዎቹ መንግሥት ባወጣው የተቀናጀ ልማት ዕቅድ ‘አዲስ አበባ ወደ ኦሮምያ እየተስፋፋች ትሄዳለች’ የሚል ሥጋት ማንሣታቸውን መግለጫው ተናግሯል፡፡
ሰልፎቹና የአደባባይ ተቃውሞዎቹ ወደ ኃይልም እየተለወጡ ብዙ ሰልፈኞች መገደላቸው፣ ብዙዎቹ የሰልፎቹ ተሣታፊዎችና የተቃዋሚዎች መሪ
ዎች መታሠራቸውንም ጠቁሟል፡፡መንግሥት የማስተር ፕላኑን ዕቅድ መሠረዙን ማክሰኞ፤ ጥር 3/2008 ዓ.ም ቢያስታውቅም ተቃውሞዎች ግን አልቆሙም በአንዳንድ የምዕራብ ሃረርጌ አካባቢዎች፣ በአምቦና በወለጋ አካባቢዎች ተቃዋሚዎች አደባባይ መውጣታቸውን፣ የመንግሥቱ ወታደሮች ጥይት መተኮሣቸውንና ተቃዋሚዎችን መደብደባቸውን መግለጫው አመልክቷል፡፡ ዝርዝር ዜናውን ከቪኦኤ ያዳምጡ።
በመግለጫው ላይ ቃላቸውን ያሠፈሩት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪካ፣ የአፍሪካ ቀንድ እና የታላላቅ ኃይቆች አካባቢ ዳይሬክተር ሙቶኒ ዋንዬኪ “የፖሊስና የወታደር እርምጃ የተከተለው መንግሥቱ በአመዛኙ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ‘ሽብርተኞች’ ሲል ታኅሣስ 5/2008 ዓ.ም ከጠራ በኋላ ነው” ብለዋል፡፡
የቪኦኤን ዘገባ ያዳምጡ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 3774

Trending Articles