“በማንኛውም ትግል ውስጥ ተማሪን ተማሪ ገደለው ሲባል ሰምቼ አላውቅም” ሲሉ ሰሞኑን በሮቤው መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተገደለው ተማሪ ሣሙኤል አባት አቶ ከተማ በቀለ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ተናግረዋል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና “… ገዥው ፓርቲ ለአንዱ እነ እንትና ናቸው እንደዚህ ያደረጉት፣ ለዚህኛው ደግሞ እንደዚያ ነው እነዚያ ናቸው እንደዚህ ያደረጉት እያሉ የግጭት ሁኔታን ለመፍጠር ከፈለገ ያስቸግራል” ብለዋል፡፡
የተገደለው ሣሙኤል ከተማ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በተወለደባት ድሬዳዋ ከተማ አጠናቅቆ ለዩኒቨርሲቲ ትምህርቱ ሮቤ ከተማ ወደሚገኘው መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ እንደሄደና የመጀመሪያ ዲግሪውን ለመቀበል የወራት ዕድሜ የቀረው እንደነበር ወላጅ አባቱ አቶ ከተማ በቀለ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ልጃቸው እርሣቸው ጋ ደርሶ ከተመለሰ አንድ ወር እንደማይሞላው ወላጅ አባቱ ለሬዲዮው ተናግረዋል
የቪኦኤዋ ጽዮን ግርማ ያጠናቀረችውን ዘገባ ያዳምጡት፡፡
↧
“ተማሪን ተማሪ ገደለው ሲባል ሰምቼ አላውቅም …” –የሟች ሣሙዔል ከተማ አባት-VOA Amharic
↧