በኦሮሚያ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ውስጥ ትልቅ መነሳሳት የፈጠረው ፍቃዱ ሹመታ በመሐበራዊ ሚዲያ እና ድረገጾች ምስሉ በሰፊው መለቀቁን ተከትሎ በመንግስት ወታደሮች ተይዞ የታሰረ ቢሆንም ትግሉን በሚደግፉ ወታደሮች ተለቆ ከአገር በመውጣት ግብፅ ካይሮ እንደሚገኝ ታወቀ።
በእስር ላይ እያለ ድብደባና የተለያዩ ማሰቃያዎች ገጥሞት የነበረው ፍቃዱ ሹመታ ” የፈለጋችሁትን ነገር ብታደርጉኝ ወደ አደባባይ ከወጣሁለት አላማ ምንም ቢሆን ወደ ኋላ እንድል አታደርጉኝም” ማለቱንና እስር ቤት ውስጥ የነበረውን ጽናት ለአሳሪዎቹ እንዳሳያቸው ምንጮች ይገልጻሉ።