ማስተር አብዲ ከድር መሐመድ ሦስት ዓለም አቀፍ የወርቅ ሽልማቶችን አግኝቷል/ Master Abdi Kedir Mohammed takes three Golden Award in 2015.
በዚህ ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት (2015) …
• 60ኛ የቴኳንዶ በዓል ሶፊያ ቡልጋሪያ ሲከበር
• ኒውዮርክ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ
• ኒውዴሊህ ህንድ ኢንተርናሽናል ማርሻል አርት ጨዋታ ላይ የሦስት ወርቅ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ማስተር አብዲ ከድር መሐመድ እስከ አሁን ድረስ የ13 ዓለም አቀፍ ሽልማት ባለቤት ናቸው፡፡ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ አስተዋውቀዋል፡፡ ለዚህ ጀግና እውቅና ክብር ለመስጠት ነገ ቅዳሜ ታህሳስ 23 ቀን 2008ዓ.ም. ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት በካፒታል ሆቴልና ስፓ(#Capital Hotel & Spa) ልዩ ዝግጅት ተዘጋጅቷል፡፡ እንግዶችም በክብር ተጠርተዋል፡፡
• ማስተር አብዲ ከድር መሐመድ – የኢትዮጵያ ዩናይትድ ቴኳንዶ አሶሴሽን መሥራችና ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ የአፍሪካ ኢንተርናሽናል ማርሻል አርት ጌም ፕሬዚዳንት እና የአፍሪካ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ምክትል ፕሬዚዳንት መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ምንጭ ጌጡ ተመስገን
↧
ማስተር አብዲ ከድር መሐመድ ሦስት ዓለም አቀፍ የወርቅ ሽልማቶች ተሸላሚ ሆነ
↧