በሃረርጌ ክፍለ ሃገር በመቻሬ እና አከባቢው ከገጠር እና ከከተማው የተሰባሰቡ ገበሬዎች እና ተማሪዎች የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እና የሃገሪቱን የከፋ አገዛዝ በመቃወም አደባባይ ለተቃውሞ ዛሬ በማለዳ በድጋሚ መውጣታቸው ታውቋል::የአንደኛ ደርጃ እና የፕሪፓራቶሪ ተማሪዎችን ያካተተው ይህ ታላቅ ተቃውሞ በከተማው ውስጥ የተስፋፋ ሲሆን የወያኔ ወታደሮች አስለቃሽ ጭስ እና ጥይት በመተኮስ ላይ ይገኛሉ::በርካቶች የቆሰሉ ሲሆን እስካሆን የሞተ ሰው ሪፖርት የለም::
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕረዝደንት ከፍተኛ አማካሪ ወንድም በህወሀት ወታደሮች ተገደሉ። አቶ ዱጉማ እሬሶ የቶ ሙክታር ከዲር ከፍተኛ አማካሪ እና የከልሉ ‘ልማት ተቋማት ቢሮ’ ሃላፊ ናቸው። ወንድማቸው መ/ር አዱኛ በሆሮ ጉዱሩ ዞን ጃርዴጋ ወረዳ አሊቦ ሁለተኛ ት/ቤት ምክትል ዳይሬክተር ነበሩ።
ትላንት ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ በጀመሩ ጊዜ ወታደሮች አንድ ተማሪ ተኩሰው መተው ወደ ሌሎች መተኮስ ሲጀምሩ ጣልቃ ገብተው ይማጻናሉ። የወታድሮቹ መልስ ግን መምህሩን ከቢሮዋቸው ጎትተው አውጥተው ተማሪዎች ፊትለፊት ግንባራቸው አሏቸው። ሁለት ሌላ መምህራንም ዳይሬክተሩን ጨምሮ ተመተው ወደቁ። መ/ር አዱኛ ላጊዜው ህይወታቸው ተርፋ ወደ ሻምቡ ሆስፒታል ተወሰዱ፣ ካዚያም ወደ ጥቁር አንበሳ ረፈራል ተላኩ። ጥቁር አንበሳ ግን ለረጅም ሰአታት እንዲጠብቁ አደረገ። እየተጠባብቁም ሳለ አንዳች ህክምና ሳያገኙ ህይወታቸው እዛው መጣባበቂያ ክፍል አለፈች። በ አሁኑ ወቅት ሬሳቸው ውደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለምርመራ ተወስዷል። ትላንት ሙክታር ከዲር ነብሰ ገዳይ ወታደሮችን አማስግኖ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው የተገደሉትን ሲኮንን እንደ ነበር ይታወሳል:: ሞት የባለስልጣናቱንም በር ማንኳኳት ጀመረች::
ምንጭ ምንሊክ ሳልሳዊ
↧
በሃረርጌ ተቃውሞ በድጋሚ ተቀስቀሰ::የፕሬዚዳንቱ አማካሪ ወንድም በአግኣዚ ወታደሮች ተገደሉ!!
↧