ፊንፊኔ ከተማን ወደ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ለማስፋፋት የተነደፈውን ማስተር ፕላንን በማቃወም
ከኦሮሞ ፖለቲካፓርቲዎች የተሠጠ መግለጫ
እኛ ስማችን ከዚህ በታች የተጠቀሰው አምስቱ የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም፡-
1. የኦሮሞ አቦ ነፃነት ግንባር
2. የኦሮሞ ነፃነት አንድነት ግንባር
3. የገዳ ሥርዓት አራማጅ ፓርቲ /ገዳ/
4. የመላ ኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና
5. የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ
የሕዝባችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥያቄዎች እንዲመለስ በሰለማዊና መንገድ እያታገል እንገኛለን፡፡
” ከአጋም ጋር የበቀለ ቁልቋል ሁልጊዜ እያደማ ይኖሯል” እንደሚባለው የኦሮሞ ሕዝብ በምኒልክ ነፍጠኞች የሀገር ባለቤትነት ከተቀማ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የኦሮሞ ወጣቶች ደም በከንቱ እየፈሰሰ ይገኛል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት መስዋህትነት የሚከፍለው ከሌሎች ጋር አብሮ ተባብሮ ለመኖር ካለው ቅን ፍላጎት ነው እንጂ የራስህን ዕድል በራስ የመወሰን ዓለም አቀፍ መርህን ተጠቅሞ ከሰሜን ገዥዎች መለየት አቅቶት አይደለም፡፡
የሕወሃት መሪዎች የፌዴራል ሥርዓትና የአገሪቱ ሕገ መንግስት ከሚፈቅደው ውጪ የመከላከያን፣ የደህንነቱን፣ የውጭ ጉዳይና የኢኮኖሚ ሴክተሩን በመቆጣጠር በኦሮሞ ጉዳይ ውስጥ ቀጥታ ጣልቃ በማግባት ፊንፊኔ ከተማ ወደ ኦሮሚያ ልዩዞን ማስፋት አለባት በማለት በያዙት ግትር አቋም የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞታል፡፡ ተማሪዎች ተቃውሞያቸውን በሰለማዊ መንገድ ስለአሰሙ ደብተርና እስክሪፕቶ እንደያዙ በጭካኔ ተገድለዋል፡፡
የኦሮሚያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በጥቅምት ወር 2008 ባደረግነው መደበኛ ስብሰባ በማስተር ፕላኑ ምክንያት አንድም የኦሮሞ ተማሪ እንዳይሞት በጋራ ተስማምተን እያለ የተማሪዎቻችን የጭካኔ ግድያ አሁንም መቀጠሉ በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡ የሕዝብ ጥያቄን በግድያ ማስቆም አይቻልም :: ስለሆነም:-
1. እኛ እናውቅላቸዋለን በማለት የሕዝብ ጥያቄን ወደ ጎን በመተው ደብተርና እስክሪፕቶ የያዙ ተማሪዎቻችን ላይ እየተፈጸመ የሚኘው የጭካኔ ግድያ ካልቆመ በአገሪቱ ሰላምና አንድነት ላይ ስጋት ፈጥሮ ነገ ልጆቻችን አብሮ ለመኖር ስለማይችሉ ግድያው በአስቸኳይ እንዲቆምና ወንጀለኞቹን ለፍርድ እንዲቀርቡ&
2. ከሕገ መንግስቱና ከፌዴራል ሥርዓት ወጪ የተነደፈው ማስተር ፕላን ለብዙ የኦሮሞ ወጣቶች ሕይወት ማጥፋትና ንብረት መውደም ምክንያት ስለሆነ በአስቸኳይ እንዲቆም እና ማስተር ፕላኑን ለማስተባበር የተቋቋመው ጽ/ቤትም እንዲዘጋ’ ኦሮሚያን እያስተዳደረ የሚገኘው ኦሕዴድም ኃላፊነቱን እንዲወጣ&
3. የኦሮሞ ሕዝብ እንደ ብዛቱና እንደቆዳ ስፋቱ በአገሪቱ ውስጥ ፍትሃዊ የሥልጣን ክፍፍል አላገኘም፡፡ በተላይ ለአንድ ፌዴራል መንግስት ቁልፍ መ/ቤት የሆኑት የመከላከያን’ የደህንነቱን፣ የውጭ ጉዳይና የኢኮኖሚ ሴክተሩን በአንድ ብሔር ቁጥጥር ስር መዋሉ አገሪቱን ወደ አለመረጋገትና መለያየት ስለሚወስድ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ39(3) መሠረት እነዚህን ቁልፍ የአገሪቱ ስልጣን ለኦሮሞ ሕዝብ እንዲሰጥ እንጠይቃለን፡፡
4. የኦሮሞ ሕዝብ አንድነቱና የሀገሩ ባለቤትነት መብት አጥቶ በየጊዜው ለከፋ አደጋ ሊጋለጥ የቻለው ዋና ምክንያት ዴሞክራሲው የገዳ ሥርዓቱ ስለፈረሰበት ነው፡፡ ስለሆነም ያልተደረጀ ሕዝብ ለድል ስለማይበቃ ከሁሉም የኦሮሚያ ዞኖች ተውጣጥተን ሕብረት የፈጠረነው’ ከ40 ዓመት በላይ ለሕዝብ በመታገል ልምድ ያካበትነውና የገዳ ሥርዓትን ለመመለስ በጽናት እየታገል ያለነው የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስር ተደራጅታችሁበሕጋዊ መንገድ መብታችሁን እንዲታስከብሩ ለኦሮሞ ሕዝብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
የሁሉም የአፍሪካ ብሔሮች መብት ከተከበረ አንድ የአፍሪካውያን ፌዴራላዊ መንግስት ማቋቋም ይቻላል!!
ፍትህ ለኦሮሞ ሕዝብ /Justice for Oromo Nation!!
ህዳር 25 ቀን 2008 ዓ.ም ‘ ፊንፊኔ
↧
አዲስ አበባ ከተማን ወደ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ለማስፋፋት የተነደፈውን ማስተር ፕላን በተመለከተ አምስቱ የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ያወጡት መግለጫ
↧