ጸረ ሙስና ኮሚሽን አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ ከኢትዮጲያ ቴሌቪዥን ባለስልጣናት ጋር ተመሳጥሮ ሊሰራው የነበረውን ሰራ ሰረዘው።
ልማታዊ አርቲስት የሚባለው ሰራዊት ፍቅሬ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን 50ኛ አመቱን ለማክበር ባወጣው ጨረታ ከባለስልጣኑ ኃላፊዎች ጋር ባደረገው መመሳጠር የቀረበውን የይስሙላ ጨረታ እንዳሸነፈ ተደርጎ የ9 ሚሊየን 411 ሺህ 600 ብር ጨረታ ያሸነፈበት ስራ በጸረ ሙስና ኮሚሽን እንዲሰረዝ ተደረገ፡፡
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን 50ኛ አመት የምስረታ በዓሉን ዝግጅት የሚያዘጋጁለት የግል ድርጅቶችን በጨረታ እንዲወዳደሩ ጋብዞ ባወጣው ጨረታ ውስጥ የተፎካከሩት ሁለት ድርጅቶች ሰራዊት ፍቅሬ ያዘጋጃቸው ድርጅቶች መሆኑ የተደረሰበት ሲሆን የይምሰል ጨረታ ተፈጽሟል ለማለት ያህል የቀረቡ እንደሆኑ የጸረሙስና መርማሪ ቡድን ባደረገው ምርመራ ደርሶበታል ።
ሠራዊት ፍቅሬ ጨረታውን እንዲያሸንፍ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ተገቢ ያልሆነ የጨረታ ሂደት ማካሄዱን የሙስና ወንጀል መፈጸሙን ያረጋገጠው ኮሚሽኑ ጨረታው እንዲሰረዝ ለጣቢያው ደብዳቤ ጽፏል።
ባለፈው ሳምንት በሰራ መቋረጡ ዙርያ ኢትዮፒካሊ ውስጥ አዋቂ ፕሮግራም ሰራዊት ፍቅሬን ጠይቆ “ውሉ ሰለመቋረጡ አላውቅም እኔ ሰራዬን እየሰራው ነው” ቢልም ፤ ጸረሙስና በደብዳቤ እንዳሳወቀው ምንጮች ገልጸውልናል።
ዛሬ ለንባብ የበቃው ቁምነገር መፅሔት ፀረሙሰና ጨረታውን መሰረዙንና ጣቢያው በራሱ ጋዜጠኞች በየክልሉ ስፖንሰሮችን በማፈላለግ በዓሉን ለማዘጋጀት ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ዘግቧል።
በፈጸመው የሙስና ወንጀል ሰራዊትም ሆነ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ባለስልጣናት መጠየቅ ቢገባቸውም እስካሁን የተመሰረተ ክስ የለም።