በኢትዮጵያ ያለዉ ሕጋዊ ስርዓት የአገዛዙ ማጥቂያ መግዣ ከመሆን ባለፈ የዜጐችን መብት አያስከብርም ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ከሰሰ።
በፍርድ ቤት ነጻ የተባሉ ተከሳሾች እንኩዋን በካድሬና በማረፊያ ቤቱ ፓሊስ ትእዛዝ መታገዳቸዉ የፍትህ ስርዓቱ በአገሪቱ የተቀበረ ለመሆኑ ማስረጃ ነዉ ሲልም ኮንኖአል።
የቪኦኤው ዘጋቢ መለስካቸዉ አመሃ ፓሪቲዉ የጠራዉን ጋዜጣዊ መግለጫ ተከታትሎ ያቀረበውን ዘገባ ያድምጡ።