Sheger FM: The Young Girl from Harar Who’s Best Friends with Wildlife..ትላንት ማምሻውን በቀረበው የሸገር ልዩ ወሬ ላይ የቀረበችው ሥሜና የመጣሁበት ቦታ አይጠቀስ ያለችው ወጣት የእንስሳት ፍቅር ብዙዎችን አጀብ አስብሏል፡፡
ሰዎችን አስተባብራ ከሕገወጥ አዘዋዋሪዎች የምታስጥላቸውን የአንበሳ ደቦሎችና የአቦሸማኔ ግልገሎች የምትንከባከበው ይህች ወጣት ውሎዋና አዳሯ ከዱር እንስሳቱ ጋር መጫወትና መላፋት ነው፡፡
ቤተሰቦቿ “አብዳለች” ቢሏትም እሷ ግን “ካበድኩም በእንስሶቹ ፍቅር ነው” ባይ ነች፡፡
“ሙዳቸውን ጠብቄ አብሬያቸው እጫወታለሁ” የምትለው ይህች የዱር እንስሳት አፍቃሪ፣ አንበሳ ንዴታም ነው ቀስ ብለህ ነው የምትቀርበው፣ አቦ ሸማኔ ቀዝቃዛ ነው ትልቅ ድመት ማለት ነው” ትለናለች፡፡
የወደፊት ሕልሟም በጫካ ውስጥ መኖር የሆነው ይህች ወጣት፣ “ትዳር ብመሰርት እንኳ አብሮኝ በጫካ ውስጥ ለመኖር የሚመርጥ መሆን አለበት” ትለናለች፡፡
የሸገር ሬዲዮ ጋዜጠኞ በወንድሙ ኃይሉ የዘጋጀውን የዚህችን ወጣት ልዩ ወሬ ያዳምጡ ።
↧
Sheger FM: The Young Girl from Harar Who’s Best Friends with Wildlife
↧