የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ከዚህ በፊት በኤርትራ ላይ የቆየውን ማዕቀብ የሚያጠብቅ ውሳኔ መውሰዱ ይታወሳል። በትናንትናው ምሽት ማዕቀቡ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም የጸጥታው ምክር ቤቱ መወሰኑ ታውቋል።
የውሳኔው መዝገብ ከዚህ በፊት በቀረቡት ክሶች ላይ ተመርኩዞ ሲሆን፣ ኤርትራ አል-ሸባብን ትደግፋለች፣ ከጅቡቲ ጋር ያልቋጨችው የድንበር ጉዳይ አለ፣ ማለትም በእአአ 2008 ያሰረቻቸውን ወታደሮች የመፍታት ክሶችን ያጠቃልላል።
የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ እንግሊዛዊው አምባሳደር ማትው ራይክፍርት (Mathew Rycroft) ውሳኔውን እንዲህ ሲሉ ገልጸዋል።
“የኤርትራና የሶማልያን ጉዳይ በተመለከተ ለየጸጥታ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት እንደተገለጸው፣ ከዚህ በፊት ተጽፎ ለውሳኔ በቀረበው የሃሳብ ሰነድ S/2015/810 ድምጽ ለመስጠት የምትፈልጉ እጃቹን አንሱ። የድምጽ አሰጣጡ ውሳኔ ይህንን ይመስላል፣ 14ቱ በመደገፍ ድምጻቸውን ሲሰጡ፣ የተቃወመ የለም። 1 ድምጸ ተአቅቦ አድርጓል። ረቂቅ ሰነዱ 22/44በመባል አልፏል” ብለው ገልጸዋል።
የኤርትራ መንግስት በበኩሉ ውሳኔውን ህግ የጣሰነ ነው በማለት አጣጥሎታል። ዝርዝሩን ከቪኦኤ ያዳምጡ።