በኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ከ150 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሞት ፣ለብዙሺዎች እስር ፣በርካቶች ቆስለውም ህዝቡ ተቃውሞውን በተለያዩ ቦታዎች ቀጥሏል።
በሳምንቱ ማብቂያ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ዛሬ ተቃውሞ እንደተካሄደባቸው ከተገለጹት አካባቢዎች መካከል፥ ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሜኤሦ ፣አሰቦት ወረዳና ምዕራብ ሸዋ ፣ይገኙበታል።ኡርፎና ሶዶም በምትባል ከሚኤሦ 8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፥ ታጣቂዎች በአርሦ አደሮች ላይ ተኩስ ከፍተው ስድስት ሰዎችን ገድለዋል።
አንድ የከተማዋ ነዋሪ ሲናገሩ ግን፥ ከተኳሾቹ መካከል አንደኛው የመንግሥት ወታደር መሆኑን አረጋግጠናል ብለዋል። በሁኔታው ሕዝቡ በጣም ተቆጥቶ ተቃውሞውን ለመግለጽም፥ ከአዲስ አበባ ጂቡቲ የሚሄደውን መንገድ ጎማና ሌሎች ቁሳቁሶችን በማቃጠል ዘግቷል ሲሉም፥ እኚሁ የከተማዋ ነዋሪ ጨምረው ለቪኦኤ ገልጸዋል።
የሚኤሦ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ መሃመድ ጀማል በሰጡት መልስ። ”የሞቱ ሰዎች አሉ። የሞቱት ግን ባካባቢው በሚኖሩ አርብቶ አደሮች በሱማሌና ኦሮሞ መካከል በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ነው ብለዋል ያለው ቪኦኤ መከላከያ ሠራዊቱ በዚያ የተገኘውም ሁለቱን ማህበረሰቦች ለማስታረቅ እንጂ በግድያው አልተሳተፈም” እንዳሉ ገልጿል።
በሚኤሦ ዛሬ ቦንብ ፈንድቶ አራት ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን ቦንቡን ያፈነዳው የመከላከያ ሰራዊት ነው በማለት የተቆጣው ህዝብ “አሸባሪው የመንግስት ወታደር ነው ህዝባችንን የሚገለውና የሚደበድበው በማለት ክልላችንን ለቆ ይውጣ”ሲሉ እማኙ ለቪኦኤ ተናግረዋል።
የሚኤሦውን የሰሙ የሀሰቦት ነዋሪዎች ስልፍ በማድረግ አጋርነታቸውን ገልጸዋል ሲሉ ነዋሪው ተናግረዋል።የሚኤሦ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ መሃመድ ጀማል “ሰላማዊ ስልፍ ያካሄዱት ያለፍቃድ ነው።እኛ እውቅና ሰጥተን የተቀበልናቸው ጥያቄዎች የሉም።ሰንመለከተው ግን ከማስተር ፕላን ጋር ጉዳዩ የተያያዘ መሆኑን ደርሰንበታል”ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።ሙሉ የቪኦኤን ዘገባ ያዳምጡ።
↧
በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው ቀጥሏል-VOA Amharic
↧